የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በራስ አቅም ሰፊ የማስፋፊያና ማሻሻያ ሥራ አከናወነ።

9

‎የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2019 በጀት ዓመት ባለፉት አራት ወራት ብቻ 2 ሺህ 472 ኪ.ሜ የኤሌክትሪክ መስመሮችን የመልሶ ግንባታ፣ የማሻሻያ እና የማስፋፊያ ሥራ ማከናወኑን አስታወቀ።

‎‎ሥራዎቹ በተቋሙ የውስጥ ፋይናንስ ብቻ የተከናወኑ መሆናቸውን የአገልግሎቱ ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አንዋር አብራር ገልጸዋል።

‎‎በዚህም በነባር መስመሮች ላይ በተከናወነው የመልሶ ግንባታና የማሻሻያ ሥራ 831 ኪሎ ሜትር ሥራ ተከናውኗል ብለዋል።

‎‎481 ትራንስፎርመሮች በከፍተኛ አቅም ባላቸው ትራንስፎርመሮች የመተካትና 411 ተጨማሪ ትራንስፎርመሮች በተለያዩ አካባቢዎች ተከላ ተደርጎላቸዋልም ብለዋል።

‎‎የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሽፋንን ለማስፋፋት በተከናወነው ሥራ ደግሞ 978 ኪሎ ሜትር መካከለኛ መስመር እና 662 ኪሎ ሜትር ዝቅተኛ መስመር በድምሩ 1 ሺህ 641 ኪሎ ሜትር አዲስ መስመር መዘርጋቱንና በእነዚህ የማስፋፊያ ሥራዎች 1 ሺህ 744 ትራንስፎርመሮች ተከላ እንደተደረገላቸው አመልክተዋል።

‎‎እነዚህ ሥራዎች በተቋሙ የውስጥ ፋይናንስ ብቻ መከናወናቸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የነባር መስመሮችን ጥራትና አቅም ለማሻሻል፣ የኤሌክትሪክ ሽፋንን ለማስፋፋት እና የአገልግሎት ተደራሽነትንና ቀጣይነትን ለማጠናከር ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል።

‎‎የመስመሮች መልሶ ግንባታና ማሻሻያ፣ የትራንስፎርመሮች አቅም ማሳደግ እና አዳዲስ መስመሮችን መዘርጋት የኤሌክትሪክ አቅርቦትን ለማጠናከር፣ የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻልና የኢንዱስትሪ፣ የንግድ፣ የግብርና እና የማኅበራዊ አገልግሎቶች ዕድገትን ለመደገፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

‎‎#የመደመር_መንግሥት!

‎

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

‎#AMECO #Red_Sea_Access #Abbay_River #Ethiopia_Sovereignty

‎#ባሕር _ዳር #ኅዳር_10_2019_ዓ_ም

‎‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article
Next articleከአረንጓዴ ዐሻራ እስከ ኮፕ 32 ፦ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዲፕሎማሲ ዓለም አቀፋዊ ምዕራፍ!