
የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልእክት፦
በሴኔጋል ዳካር በተካሄደው የ2026 የዓለም ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ኢትዮጵያን በዓለም የአትሌቲክስ ሜዳሊያ ሰንጠረዥ በአንደኝነት እንድታጠናቅቅ ያስቻሉትን ታዳጊ አትሌቶቻችንን በአካል አግኝቼ አበረታትቻለሁ።
በአፍላ ዕድሜያችሁ በዓለም መድረክ ባሳያችሁት ብቃትና ባስመዘገባችሁት ድል የሀገራችሁን ሰንደቅ በክብር ከፍ አድርጋችኋል።
ለመላው ኢትዮጵያውያን ደስታና ኩራት፣ ለታዳጊው ትውልድም ታላቅ ተስፋና ተምሳሌት ሆናችኋል።
የአሁኑ ድላችሁ ለነገ የላቀ ስኬት መነሻና መሠረት ነው። በራሳችሁ እመኑ፤ ህልማችሁን አሳድጉ፤ ከዛሬው ድል የበለጠ ከፍታን አልሙ።
ለመጪዎቹ የዓለም ሻምፒዮናዎችና ኦሎምፒክ ጨዋታዎች በበለጠ ብቃት፣ በትጋትና በቁርጠኝነት ተዘጋጁ።
መንግሥት በቀጣይ የስኬት ጉዟችሁ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል።
እናንተም ብቃትና ችሎታችሁን በቀጣይነት እያዳበራችሁ፣ ህልማችሁን እያሳደጋችሁ የሀገራችሁን ስምና ሰንደቅ በዓለም አደባባይ በተከታታይ ከፍ ለማድረግ በጽናት ለድል እንድትሰለፉ አደራ እላለሁ።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ኅዳር_09_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
