
ከጨዋታው 2 ሰዓት ቀድመው ሜዳ ላይ ተገኝተዋል። ከ90 ደቂቃ በላይ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ብሔራዊ ቡድናቸውን አነቃቅተዋል። እንደ 12ኛ ተጫዎች ኾነው የተጋጣሚ ቡድንን አስጨንቀዋል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ደጋፊዎች።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም በመገኘት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ብድን ከሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ ታድመዋል።
ደጋፊዎች በኅብር ከቀመጫቸው ተነሱ” ውብ ሀገሬ በአንች እኮ ነው መከበሬ” ተከታታይ ከስታዲየሙ ዳር እስከ ዳር አስተጋባ።
በአንድነትም ተቃቀፉ ” ተከብረሽ የኖርሽው በአባቶቻችን ደም፣ እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” እያሉ ስታዲየሙን በጩኸት አናጉት።
ተጫዋቾች ወደ ሜዳ ሲገቡ ጭብጨባ እና አድናቆት ፈሰሰ። ድል የተራበው ደጋፊ “ውጤት ውጤት ውጤት” ሲል በአንድነት መልእክቱን አስተላለፈ።
ስፖርታዊ ጨዋነት፣ የሀገር ፍቅር፣ በሠንደቅ ዓላማ ታጅቦ ታይቷል። የኳስ ፍቅር፣ የድል ርሃብ፣ የአሸናፊነት ፍላጎት እና መንፈስ በደጋፊው ገጽ ላይ ተነቧል። የዘንባባዋ ከተማ ባሕርዳር በደጋፊዎች ከፍተኛ ድምጽ ደምቃ ውላለች።
ባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተደጋጋሚ የአፍሪካ ዋንጫን ማስተናገዷ የቱሪዝም እንቅስቃሴዋ እንዲነቃቃ አድርጓል። የስታዲየሙ ዘመናዊነት ለደጋፊዎች ምቹ መቀመጫን ፈጥሮላቸዋል። ሙሉ ደቂቃውን በምቾት እንዲደግፉ አድርጓቸዋል።
ከባሕር ዳር ከተማ ነዋሪዎች በተጨማሪ ጨዋታውን ለመመልከት የመጡ እንግዶች የዘንባባዋን ከተማ ውበት ተመልክተዋል። የደጋፊውን ትጋት አይተዋል። አብረው በፍቅር ለብሔራዊ ቡድናቸው ድጋፍ ሰጥተዋል።
የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሥራ መጀመር የከተማዋን የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንዲነቃቃ ያስችላል።
#የመደመር_መንግሥት!#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ሕዳር_08_2019_ዓ_ም
✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
