ባሕር ዳር ዛሬ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታ ታስተናግዳለች!

8

በ2027 ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ 4ኛ የምድብ ጨዋታ ዛሬ ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሞዛምቢክ ጋር በባሕር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ይጫወታል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዛሬው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን በባሕር ዳር ስታዲየም አከናውኗል።

በጨዋታው ብሔራዊ ቡድናችን አረንጓዴ ማልያ፣ ቢጫ ቁምጣ እና ቀይ ካሶተኒ ፣ የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን ቀይ ማልያ፣ ጥቁር ቁምጣ እና ጥቁር ካሶተኒ ለብሰው ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ጨዋታውን ጋምቢያዊው ንፋሊ ጃርጁ የሀገሩ ዜጎች ከሆኑ ረዳቶቹ ጋር በዳኝነት ይመራል።

#ባሕር_ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም

‎#የመደመር_መንግሥት!

‎‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

‎‎#EthiopiaPrevails #AfricanIndependence #AMECO

‎‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም

‎‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous article‎የዓባይ ጌጥ የጣና ሙሽራዋ ባሕር ዳር