‎የዓባይ ጌጥ የጣና ሙሽራዋ ባሕር ዳር

5

🌴‎‎ባለዘንባባዋ ከተማ ባሕር ዳር ተፈጥሮ ባስጌጠው ውበቷ ላይ የኢትዮጵያ ከተሞችን መልክ የገለጠው የኮሪደር ልማት ተወዳጅ ከተማ አድርጓታል፡፡

ባሕር ዳር ከተማ በኮሪደር ልማቱ ውበቷ እጥፍ ድርብ ጎልቶ የነዋሪዎቿንና የጎብኚዎችን ቀልብ እየሳበችም ትገኛለች።

‎የኮሪደር ልማቱ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል። ‎ሰፋፊና ውብ መንገዶቿ እስከ ምሽት የሚናፈቁ ኾነዋል። የጣና ሐይቅ ዳርቻ ለሰዎች እንቅስቃሴ ምቹ እና ኹነኛ መዝናኛ ተደርጓል። ብስክሌት ሌላው መገለጫዋ ለኾነችው ባሕር ዳር ምቹ መንገድ ተገንብቶላታል። ጣናን እንደልብ ለማየትና በተፈጥሮ ውበት ለመደመም አካባቢው ውብና አመቺ በሆነ መልኩ ተሻሽሏል። ዘመናዊው የዓባይ ድልድይ የውበት መገለጫዋ ሌላ በረከት ኾኖላታል።

‎‎በወንበር 52 ሺህ ተመልካቾችን እንዲይዝ ተደርጎ የሠራው የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዓለም አቀፍ መስፈርትን በማሟላቱ ለብሔራዊ ቡድናችን ኩራት ኾኗል፡፡

‎‎በኢትዮጵያ ሁለተኛው ውብና ግዙፍ የአየር መንገድ ተርሚናል የተገነባላት ባሕርዳር ለቱሪስቶች ይበልጥ ምቹ መዳረሻ አድርጓታል።

‎‎በየዓመቱ የሚካሄደው ታላቁ የጣና ፎረም ጉባኤ ባሕር ዳር ትልቅ የዲፕሎማሲ አቅም የመሆን ዕድልን ፈጥሮላታል።

‎‎ባሕር ዳር በዙሪያዋ እንደ ጎርጎራ ያሉ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች በመገንባታቸው ለቱሪስቶች መሸጋገሪያ የምትሆንበት ዕድልን ፈጥሮላታል፡፡ በጣና ሐይቅ ላይ የሚንሸራሸሩት ፈጣንና ቅንጡ ጀልባዎች ባሕር ዳርን የምትወደድና ባለብዙ አማራጭ መዝናኛ እንድትኾን አስችሏታል።

‎‎በከተማዋ የተተገበረውና እየተስፋፋ የሚገኘው የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ባሕር ዳር ዘመኑን የዋጀች ከተማ አድርጓታል።

‎‎መሰረተ ልማቶችን ያስተሳሰረው የባሕር ዳር ኮሪደር ልማት አሁን ባለው አሠራር የመንገድ፣ የውኃ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ፣ የኤሌክትሪክ እና የቴሌኮም መስመሮች በአንድ ማዕቀፍ ስር አቀናጅቷል፡፡ በአንዱ ተሠርቶ በሌላው የሚፈርስበትን የሀብት ብክነትም አስቀርቷል።

‎‎የባሕር ዳር አዲስ መልክ በአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ከተሞች እስከ ምሽት ድረስ የመሥራት ልምድ በመዳበሩ አዲስ እና ጠንካራ የሥራ ባሕል እንዲጎለብት አድርጓል፡፡ የተሠሩት ማሻሻያዎች ለግል ባለሀብቶች እና ለአነስተኛ ነጋዴዎች አዳዲስ እና የተለያዩ የንግድ አማራጮችን አስገኝተዋል።

‎‎የኮሪደር መንገዶቹ መዘርጋት ምርት እና አገልግሎት በቀላሉ እንዲንቀሳቀስ በማድረግ በከተማዋ የተሻለ እና ፈጣን የገበያ ትስስር ፈጥሯል። ባሕር ዳር በኮሪደር ልማት ቆንጅታለች፤ ቁንጅናዋ ለብዙዎች የገቢ ምንጭ ሆኖላቸዋል፡፡

‎‎ባሕር ዳር ተፈጥሮ፣ ባሕል፣ ጥበብ፣ ዘመናዊነት፣ መንፈሳዊነት፣ አምራችነት እና አብሮነት ተዋሕደው የፈጠሯት የምድር ጌጥ ናት።

‎‎‎#የመደመር_መንግሥት!

‎‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

‎‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_08_2019_ዓ_ም

‎‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

 

 

Previous articleብርድ እና ሐሩር የማይበግረው፣ ዳገት ቁልቁለት የማይገድበው የሉዓላዊነታችን ጋሻ!