“የባንዳዎች ትብብር ያልበገረው የኢትዮጵያ ድል አድራጊነት ከፍታ!”

21

ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ጅኦፖለቲካዊ የበላይነትን ለማስጠበቅ ስትል የውስጥ ሰላምን ለማናጋት እና የልማት ፕሮጀክቶችን ለማደናቀፍ ለዘመናት ስትሰራ መቆየቷን ታሪክ የማይሽረው ዘመን የማይረሳው ሐቅ ነው።

የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚገልጹት ግብጽ በታሪክ ኢትዮጵያ የተረጋጋች እና በምጣኔ ሀብት ጠንካራ ሀገር እንዳትሆን በቀጣናው ከሚገኙ የተለያዩ አጋር ኃይሎች በመተባበር ጫና ስታደርግ ቆይታለች።

ዛሬም ለኤርትራ (ሻዕቢያ) እና ለሌሎች የውስጥ አማጺ ቡድኖች ወታደራዊ እና የሎጅስቲክ ድጋፍ በማድረግ ኢትዮጵያን በእጅ አዙር ጦርነት ለማዳከም ጥረት እያደረገች ትገኛለች።

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ እና በግብጽ መካከል ላለው የዲፕሎማሲ ውጥረት ዋነኛ ማዕከል ሆኖ ቆይቷል።

ኢትዮጵያ ከ85 በመቶ በላይ የዓባይን ውኃ የምታመነጭ ሀገር እንደመሆኗ መጠን ሕዝቧን ከድህነት ለማውጣት በወንዟ የመጠቀም ተፈጥሯዊ እና ሕጋዊ መብት ቢሮራትም በግብፅ ሴራ ስትፈተን ቆይታለች።

ኢትዮጵያ ምንም እንኳን በታሪካዊ ጠላቷ ግብጽ በኩል ዲፕሎማሲያዊ ጫና እና ፖለቲካዊ ሴራ ቢበዛባትም በራሷ አቅም ግድቡን እውን በማድረግ ፍትሐዊ የውኃ አጠቃቀም መርሕን በተግባር አረጋግጣለች።

“ግብጽ” ኢትዮጵያ በስህተት ያጣችውን ጥንታዊ እና ታሪካዊ ባሕር በር ባለቤትነት እንዳታገኝ ዛሬም እንደትላንቱ የዲፕሎማሲ እንቅፋት እየፈጠረች ትገኛለች።

ይሁን እንጅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እንዳሉት ኢትዮጵያ እያደገ የመጣውን የሕዝብ ቁጥር እና ኢኮኖሚ ለመሸከም አስተማማኝ የባሕር በር ማግኘት የሕልውና ጉዳይ ነው።

የኢትዮጵያ መንግሥት ይህን ጥያቄ በሰላማዊ እና በጋራ ተጠቃሚነት መርሕ ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን በአጽንኦት ገልጸዋል።

ትዮጵያ የውስጥ እና የውጭ ፈተናዎች ሳይበግሯት ትኩረቷን በኢኮኖሚ ማሻሻያ እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ማድረጓንም ተናግረዋል።

በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በታዳሽ ኃይል አቅርቦት እና በቀጣናዊ የመሠረተ ልማት ትስስር እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶችም ሀገሪቱ በምሥራቅ አፍሪካ ጠንካራ የኢኮኖሚ እና የጂኦፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሀገር እንድትሆን የሚያስችሏት መሆናቸውን ገልጸዋል።

• ​#ኢትዮጵያ #የሕዳሴግድብ
• ​#GERD#የባሕርበር
• ​#የግብጽሴራ

የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_06_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየጥፋት ሴራዎችና የኢትዮጵያ ያልተቋረጠ የበላይነት
Next article“የሻቢያ የጥፋት ሴራ ከሽፏል፤ የኢትዮጵያ ኀያልነት ከፍታው ላይ ነው!”