ለጠላት እንደ ሰማይ ከፍታ የከበደው የኢትዮጵያ አይበገሬነት።

8

ግብጽ ኢትዮጵያን ለማዳከም፣ የውስጥ ሰላምን የመንሳት እና የጥፋት ኀይሎችን የማደራጀት እና የማስታጠቅ ስትራቴጂን በዘመናት ውስጥ ስትከተል ኖራለች።

የግብጽ የጠላትነት ጥግ ዛሬም ድረስ በግልጽ የሚታይ ነው። የግብጽ ዋና አላማ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ እንዳትለማ፣ በአካባቢው ላይ ያላት ጂኦፖለቲካዊ ተጽዕኖ እንዳይጠናከር እና በውስጣዊ ቀውሶች ተጠምዳ እንድትኖር ማድረግ ነው።

ፕሮፌሰር ሀጋይ ኤርሊኽ እንደሚሉት ግብፅ የኢትዮጵያን የውኃ ልማት እንደ ህልውና ስጋት ትወስደዋለች። የውስጥ ሰላሟ ለመረበሽ ከኢትዮጵያ በተቃራኒ ከቆሙ የሀገር ውስጥ አጥፊ ኀይሎች ጋር ምስጢራዊ ግንኙነት በመፍጠር የገንዘብ፣ የዲፕሎማሲ እና የመሳሪያ ድጋፍ ስታደርግ ኖራለች።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ከማንም ጋር ጦርነት እንደማትፈልግ እና በጋራ ተጠቃሚነት እንደምታምን አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ እድገቷን እና ሉዓላዊነቷን ለመገዳደር የሚደረጉ ማናቸውም ሴራዎች ተቀባይነት የላቸውም።

ኢትዮጵያን የማንበርከክም ኾነ የብልጽግና ጉዞዋን የማስተጓጎል አንዳንዶች የሚመኙት ህልም ከሰማይ ከፍታ በላይ የከበደ ነው። የውጭ ኀይሎች ኢትዮጵያን ለማዳከም የሚያደርጉት ጥረት የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት ይበልጥ ያጠናክሩታል።

የግብጽ ስልታዊ አካሄድ ኢትዮጵያ በጋራ ጥቅም ላይ ተመሥርታ የምታደርገውን የልማት ጥረት እንደ ስጋት በመቁጠር የጥፋት መንገዶችን መከተሏ ነው። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የዚህ የጠላትነት ሰለባ አንዱ ማሳያ ነው።

ግብጽ በዲፕሎማሲው መስክ በዓለም አቀፍ ተቋማት እና በድብቅ በሚደረጉ የጸጥታ መዋቅር ድጋፎች ኢትዮጵያን ለመፈተን ብትሞክርም የኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ግን ከዚህ ሁሉ ፈተና በላይ በመኾን የልማት ሥራዎቹን አጠናክረው ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ አይበገሬነት የሚገለጸው በታሪክም ኾነ በዘመኑ በውጭ ኀይሎች የሚሰነዘሩባትን ጫናዎች በአንድነት እና በፅናት በመመከት ረገድ በሚታየው የሕዝብ እና የሀገር ፍቅር ነው።

የግብጽ ክፋት እና ሴራዎች ውስብስብ ቢኾኑም የኢትዮጵያ ጽኑ መሠረት፣ የሕዝቧ አንድነት እና የሰላም ፍላጎት ከማንኛውም የጥፋት ኀይል የላቀ በመኾኑ ሀገሪቱ በጽኑ የልማት ጎዳና ላይ እንድትቀጥል አስችሏታል።

#Ameco ​#StrongerTogether #Sovereignty #Ethiopia

የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_06_2019_ዓ_ም

በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየኢትዮጵያን ግስጋሴ ያላስቆመው የግብፅ ሴራ!