
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን አስደናቂዎቹ የደብረ ሮሐ ቅዳስ ላሊበላ ውቅር ዐቢያተክርስቲያናት የይገኛሉ። ቤተ ጊዮርጊስ ከአስደናቂዎቹ የላሊበላ ዐቢያተክርስቲያናት መካከል አንዱና ልዩ የኪነ ህንጻ ጥበብ ያረፈበት ነው።
ላሊበላ ከተማ አስደናቂውን ቤተጊዮርጊስ ጨምሮ በውስጧ በሚገኙት እጹብ ድንቅ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ምክንያት በዓለም መድረክ ከታላላቅ ከተሞች በላይ ስሟ የገነነ እና ለጉብኝት ተመራጭ ከተማ ናት፡፡
በየዓመቱ ታኅሣሥ 29 ቀን የሚከበረውን የልደት በዓል ለመታደምም በርካቶች ወደ ዚህ ድንቅ ሥፍራ ላሊበላ ያቀናሉ። በርካቶችም በዚህ ወቅት በእግራቸው ወደ ቅዱሱ ቦታ ለመድረስ ጉዞ ያደርጋሉ።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!
