ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፋይናንስ ውይይቶች ላይ የመሪነት ሚናዋን አጠናክራ ቀጥላለች

2

የገንዘብ ሚኒስትር እና የCOP32 ዋና ተደራዳሪ ፍጹም አሰፋ (ዶ.ር) በCOP31 ከባኩ እስከ ቤለም የተዘረጋውን ፍኖተ ካርታ ለመተግበር እና ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ፋይናንስ ግቦችን ወደ ተጨባጭ ስራ ለመቀየር በተካሄደ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

ውይይቱም ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ቃል-ኪዳኖችን ከታዳጊ አገራት ተጨባጭ ሁኔታና የፋይናንስ ፍላጎቶች ጋር ማጣጣም ያለውን አስፈላጊነት አጉልቶ አሳይቷል።

ይህም ተመጣጣኝና ተደራሽ የሆነ የፋይናንስ ድጋፍ ማግኘትን፣ ጠንካራ ተቋማትን መገንባትን እና የበለጠ ውጤታማ የአፈጻጸም ሂደትን ማረጋገጥን ያካትታል።

ኢትዮጵያ የመጪው COP32 አስተናጋጅ ሀገር እንደመሆኗ መጠን፣ በዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ሂደት ውስጥ ተሳትፎዋን በቀጣይነት እያጠናከረች ትገኛለች።

በዚህም የአየር ንብረት ዕቅዶችን ከተግባራዊ አፈጻጸም፣ ፋይናንስን ደግሞ ከተጨባጭ ውጤት እንዲሁም ዓለም አቀፍ ቁርጠኝነቶችን በተግባር ከሚረጋገጡ ትግበራዎች ጋር ለማገናኘት የሚያስችሉ ተግባራዊ አሰራሮችን በማመላከት ተሳትፎዋን ትርጉም ባለው ቀጣይነት እያጠናከረች ትገኛለች።

#COP31 #COP32 #ClimateAction #ClimateFinance

Previous articleበሰማይ ፣ በባሕር እና በምድር የተዘረጋው የኢትዮጵያ ክንድ!