ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ለኮፕ 32 ዝግጅት በጋራ እንደሚሰሩ ገለጹ

5

አዲስ አበባ: ሕዳር 03/2019(አሚኮ) ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ለኮፕ 32 ዝግጅት ትብብራቸውን እንደሚያጠናክሩ አስታወቁ።

31ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 31) በቱርኪዬ አንታሊያ እየተካሄደ ይገኛል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኮፕ 2 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከጉባኤው ጎን ለጎን፣ ከሩዋንዳ ሪፐብሊክ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር በርናዴት አራክዊዬ (ዶ/ር) ጋር ለኮፕ 32 ዝግጅት ትብብርን ለማጠናከር ሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ሁለቱ ወገኖች በጋራ ቅድሚያ በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በቅርበት ለመሥራትና ለሁሉም አካላት ትርጉም ያላቸው ውጤቶችን የሚያስገኝ የተሳካ ኮፕ 32 እንዲኖር ጥረቶቻቸውን ለማስተባበር ተስማምተዋል።

#COP31 #COP32 #ClimateAction

Previous articleየገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር ) ከዓለም ባንክ ቡድን ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ