‎የደሴ ከተማ እና አካባቢዋን የኀይል አቅርቦት በ12 እጥፍ የሚያሳድገው የኀይል ማከፋፈያ ጣቢያ ሊጠናቀቅ ተቃርቧል።

8

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል የደሴ ከተማ እና አካባቢዋን የኀይል አቅርቦት ችግር የሚቀርፍ ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኀይል ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክትን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ እየሠራ ነው።
‎
‎በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል የደሴ ፕሮጀክት ሥራ አሥኪያጅ በሪቻ ሚንታሳ ፕሮጀክቱ የአካባቢውን የኀይል እጥረት እና መቆራረጥን ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ አሥተማማኝ የኀይል አቅርቦትን ለከተማው እና ለአካባቢው ለማቅረብ ወደ ግንባታ መገባቱን ተናግረዋል።
‎
‎ፕሮጀክቱ የአካባቢውን የኀይል አቅርቦት በ12 እጥፍ የሚያሳድግ መኾኑንም ገልጸዋል። ፕሮጀክቱን በሁለት ዓመት ለማጠናቀቅ ታስቦ ሥራ መጀመሩንም አንስተዋል።
‎
‎ግንባታው የኀይል ማከፋፈያ እና የኀይል ማስተላለፊያ ሁለት ፕሮጀክቶችን እንደያዘም ገልጸዋል።
‎
‎ሥራውን ለማጠናቀቅ የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች መግባታቸውንም አንስተዋል።
‎
‎ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በደሴ ከተማ እና በዙሪያው ለሚገኙ ወረዳዎች አስተማማኝ ኀይል ከማቅረብ በተጨማሪ በኮምቦልቻ ከተማ በሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ያለውን የኀይል ጭነት ለማቃለል ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ተብሏል።
‎
‎#የመደመር_መንግሥት!
‎
‎#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #ኅዳር_03_2019_ዓ_ም
‎
‎✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
‎
‎የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🇪🇹​የአፍሪካን ገጽታ የቀየረው የኢትዮጵያውያን አንጡራ ሀብት፦ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ!