
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ መሐሙድ ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼህ መሐሙድ ጋር ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ቀደም ብሎ ተገናኝተናል ብለዋል።
በሶማሊያ ወቅታዊ የደኅንነት ሁኔታና ሰፋ ባሉ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ሃሳቦችን መለዋወጣቸውን ገልጸዋል። የቀጣናውን ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈን ቀጣይነት ያለው ውይይትና ትብብር አስፈላጊ መኾኑን አጽንኦት ሰጥተናል ነው ያሉት።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
