የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር በረከት ፍስሐጽዮን ከዓለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ሴሌስቴ ሳውሎ ጋር ተወያዩ።

9

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር በረከት ፍስሐጽዮን ከCOP31 ጉባኤ ጎን ለጎን ከዓለም አቀፉ የሜትሮሎጂ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ፕሮፌሰር ሴሌስቴ ሳውሎ ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው በየአየር ንብረት እና የአየር ሁኔታ ምልከታ ሥርዓቶች ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር፣ የቅድመ ማስጠንቀቂያ አቅሞችን ማሳደግ፣ የአየር ንብረት መረጃዎችን ፍትሀዊ ተደራሽነት ማበረታታት እና በአዲስ አበባ ከሚካሄደው COP32 በፊት በሳይንስ ላይ የተመሰረተ የአየር ንብረት ጥበቃን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

ውይይቱ በጠንካራ የምልከታ አውታረ መረቦች፣ በመረጃ ፍትሐዊነት፣ በአቅም ግንባታ እና በዓለም አቀፍ ትብብር አማካኝነት የመቋቋም አቅምን ለማጠናከር ያለውን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጧል።

#COP31 #COP32Ethiopia #WMO #ClimateAction

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ኅዳር_01_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየወባ በሽታ እየፈተናት ያለችው ባሕር ዳር!
Next articleየ99% የድል ማብሰሪያ፡ የኢትዮጵያ ቡና ለአውሮፓ ህብረት መመሪያ (EUDR) የሰጠው አሸናፊ ምላሽ አዲስአበባ ፡-የደን ጥበቃና የቡና ኤክስፖርት፡ የኢትዮጵያ ታሪካዊ የበላይነት ለአውሮፓ ገበያ