
መሥተዳድር ምክር ቤቱ በዋናነት ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ከ2 ነጥብ 65 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ለ16 አልሚዎች በክልሉ እንዲያለሙ የመሥሪያ ቦታ በምደባ እንዲሰጥ ውሳኔ አስተላልፏል።
የመሥሪያ ቦታ እንዲሰጥ ውሳኔ የተላለፈውም ልዩ ሀገራዊና ክልላዊ ፋይዳ ባላቸው በተለይ በሆቴልና ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና ማኑፋክቸሪን፣ የእርሻና ምርት ማቀነባበሪያ፣ በቅይጥ አገልግሎትና በሆስፒታል እንዲሁም በመዝናኛ ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ነው።
የመሬት ምደባ የተደረገላቸው ባለሃብቶች በሚሰማሩበት የልማት መስክም ሀገራዊና ክልላዊ ፋይዳ ያላቸውና ሕዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስለመሆናቸው ተጠቁሟል።
መሥተዳድር ምክር ቤቱም ለባለመብቶቹ የተሰጠው መሬት ለተፈለገው ልማት በማዋል በአፋጣኝ ወደ ሥራ እንዲገቡ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በአጀንዳው ጥልቅ ውይይት ያካሄደው መሥተዳድር ምክር ቤቱ ውሳኔውን በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል።
የክልሉ መንግሥት የኢንቨስትመንት ዘርፉን የበለጠ ለማነቃቃት በትኩረት እየሠራ መሆኑም ተመላክቷል።
በቀጣይም ሀገራዊ ፋይዳ ባላቸውና የሕዝብን ተጠቃሚነት በሚያጎለብቱ ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል።
መሥተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
