
የአዋሽ- ኮምቦልቻ- ሃራ ገበያ የባቡር መስመር የኃይል አቅርቦት ፕሮጀክት ግንባታ እየተካሄደ መኾኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል።
በፕሮጀክቱ 202 ነጥብ 15 ኪሎ ሜትር የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ይዘረጋል ተብሏል።
አሁን ላይ የ106 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትሩ ዝርጋታ፣ ከ552 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች የ440 የመሠረት ሥራ እና የ338 ምሰሶዎች ተከላ ተጠናቅቋል ነው የተባለው።
በተጨማሪም የመተሃራ፣ ደብረ ብርሃን፣ ሸዋሮቢት እና ከሚሴ ማከፋፈያ ጣቢያዎች የማስፋፊያ፣ የሙከራ እና የፍተሻ ሥራዎች ተከናውነዋል።
ለስምንት የባቡር ትራክሽን ጣቢያዎች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እየተከናወነ ባለው ሥራ ትራክሽን 1 እና 2 ከመተሃራ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል የሚያገኙበት ሥራም ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ተገልጿል።
ጣቢያዎቹ ከመተሃራ በተጨማሪ ከደብረ ብርሃን ማከፋፈያ ጣቢያ በአማራጭ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ የምሰሶዎች የመሠረት እና ተከላ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።
ለቀሪዎቹ ትራክሽን ጣቢያዎች የቅየሳ፣ ዲዛይን፣ የዕቃ አቅርቦት እና የካሳ ክፍያ ሥራዎች መጠናቀቃቸው ተገልጿል።
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው ተቋሙ አጠቃላይ የፕሮጀክቱን ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ አቅዷል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_27_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
