“ኢትዮጵያ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ በኩል የምትሰጠውን ሥልጠና በአህጉሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጓን ትቀጥላለች” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

8

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ‎“ለዕድገት መምራት” በሚል መሪ መልዕክት ዛሬ መካሔድ በጀመረው 2ኛው የአፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤ ላይ በመገኘት ንግግር አድርጌያለሁ ነው ያሉት።

የአፍሪካ መዲና የኾነችው አዲስ አበባ ይህንን ታላቅ አህጉራዊ መድረክ ማስተናገዷ ለሁላችንም ታላቅ ኩራት ነው ብለዋል።
‎
‎በመደመር እሳቤ እየተመራን፤ ሕዝባዊ አንድነትን፣ ተጠያቂነትን እና አካታች አሥተዳደርን ማረጋገጥ የፖለቲካ አመራር የዜጎችን ሕይወት እንዲያሻሽል የሚያስችሉ ወሳኝ መሠረቶች ናቸው።

ይህም ፓርቲዎች ከምርጫ ውድድር ባለፈ አሻግረው እንዲመለከቱ፣ በመንግሥት ለውጦች የማይቀያየሩ፣ ብሔራዊ እና ቅድሚያ በሚሰጣቸው የረጅም ጊዜ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ እና ለሀገር ጥቅም በጋራ እንዲሠሩ ይጠይቃል።
‎
‎በሌላ በኩል ተተኪው ትውልድ ኃላፊነቶችን እየወሰደ የሚያድግበትን ዕድሎችን እያገኘ እንዲሄድ ለማድረግ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እጅግ ወሳኝ ጉዳይ ነው።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ አመራር የልህቀት አካዳሚ በኩል የምትሰጠውን ሥልጠና በአህጉሪቱ ለሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክፍት ማድረጓን ትቀጥላለች ብለዋል።
‎
‎ለሕዝባችን የተሻለ መጻኢ ዕድል የመገንባት ኃላፊነታችን ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት በመልዕክታቸው።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_27_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበፋርጣ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር ተወያዩ።