በፋርጣ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ነው።

6

 

በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ ወደ ማኅበረሰቡ እየተቀላቀሉ ነው።

የፋርጣ ወረዳ ሰላም እና ጸጥታ ጽሕፈት ቤት ምክትል ኀላፊ ሀምሳ አለቃ ማሩ አድማስ ለአሚኮ እንደገለጹት
በአካባቢው እየተሠራ በሚገኘው ጠንካራ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ እና ጠንካራ የሕግ ማስከበር እርምጃ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እየሄዱበት ያሉት መንገድ ትክክል አለመኾኑን በመገንዘብ ወደ ሰላም እየተመለሱ ነው ብለዋል።

በአካባቢው የሚገኘው የጸጥታ ኀይልም ወደ ሰላም የተመለሱ ታጣቂዎችን እየተቀበለ መኾኑን ተናግረዋል።

የሰላም አማራጭን ለሚቀበሉ ታጣቂዎችም አስፈላጊው እንክብካቤ እየተደረገላቸው መኾኑንም ገልጸዋል።

የተሀድሶ ሥልጠና በማስገባት ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ፣ ፍላጎት ያላቸውን ወደ ወረዳው የጸጥታ መዋቅር በማካተት ለሰላም እንዲሠሩ እና ማኅበረሰባቸውን እንዲክሱ እየተደረገ መኾኑንም አብራርተዋል።

የወረዳውን የጸጥታ መዋቅር በማጠናከር እና ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በማቀናጀት የወረዳውን ሰላም ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው ብለዋል።

#የመደመር_መንግሥት!

#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_27_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleከኢኮኖሚ ባሻገር፡- የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት በቀጣናዊ ጸጥታ እና ሉዓላዊነት ሚዛን!