
ክልላዊ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በደሴ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በክልሉ አሻጋሪ የልማት ግቦች የተመላከቱ የልማት፣ የመልካም አሥተዳደር እና የሰላም ግንባታ ሥራዎች ላይ በስኬት የሚነሱ ተግባራት መከናዎናቸውን ገልጸዋል።
በውስንነት የሚነሱ ተግባራት መኖራቸውንም አንስተዋል።
በእንስሳት ሀብት ልማት፣ በሥራ አጥነት ምጣኔ ቅነሳ፣ አነስተኛ ኢንተርፕራይዞችን በማጠናከር፣ በቤት ልማት እና በሰው ሀብት ልማት በመልካም አፈጻጸም የሚጠቀሱ ሥራዎች መሠራታቸውንም ተናግረዋል።
የምርት ትስስር፣ የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች ትስስር፣ የትምህርት ጥራት እና ተሳትፎ በክፍተት የተገመገሙ ተግባራት እንደኾኑም ገልጸዋል።
በሰላም መደፍረስ የተሸፈነን የሌብነት ተግባር በቁርጠኝነት መታገል እንደሚገባ ያነሱት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ የክልሉ ሰላም እና መረጋጋት የሁሉም ሥራዎች መሠረት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል ነው ያሉት።
በየደረጃው የሚገኙ የሥራ ኀላፊዎች ሕዝብ የሰጣቸውን አደራ በተጠያቂነት ለመወጣት በሩብ ዓመቱ በክፍተት የታዩ ሥራዎችን ከነምክንያቶቻቸው በመለየት ለቀጣይ ሥራዎች የተለየ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
በመድረኩ የሩብ ዓመቱ አፈጻጸም በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አስተባባሪ ዘሪሁን ፍቅሩ (ዶ.ር) ቀርቦ ምክክር እየተደረገበት ይገኛል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ደሴ #ጥቅምት_26_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ አንተነህ ፀጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
