የኢትዮጵያ ብሔራዊ የድንገተኛ ሕክምና ቡድን ዓለም አቀፍ ምደባ አገኘ።

10
ኢትዮጵያ ብሔራዊ የድንገተኛ ሕክምና ቡድኗ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የማረጋገጫ ሂደትን በማጠናቀቅ መስከረም 2026 ዓ.ም ዓለም አቀፍ ምደባ አግኝቷል። ስኬቱ በአዲስ አበባ በተካሄደው 7ኛው የድንገተኛ ሕክምና ቡድኖች (EMT) ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይ ይፋ ኾኗል። ጉባኤው በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ክልል ሲካሄድ የመጀመሪያው መኾኑም ተጠቁሟል።
የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የተገኘው ዓለም አቀፍ ምደባ የጤና ባለሙያዎች እና ተቋማት የጋራ ጥረት ውጤት መኾኑን ገልጸው ደረጃውን ማስጠበቅ እና የክልሎችን የድንገተኛ ምላሽ አቅም ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ክልል ዳይሬክተር ዶክተር ሙሐመድ ያኩብ ጃናቢ፣ የአፍሪካ የጤና ሥርዓትን እና የሀገራትን ትብብር ማጠናከር ለድንገተኛ የጤና አደጋዎች ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት ወሳኝ መኾኑን አመላክተዋል። አፍሪካ በድንገተኛ አደጋ ምላሽ ረገድ ታሪክ እየሠራች መኾኗንም ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር መልካሙ አብቴ የተገኘው ምደባ በተፈጥሮ አደጋዎች፣ በበሽታ ወረርሽኞች እና በሌሎች የጤና አደጋዎች ወቅት ፈጣን እና ውጤታማ ምላሽ ለመስጠት የሀገሪቱን አቅም የሚያጠናክር መኾኑን ጠቁመዋል።
የተገኘውን ዓለም አቀፍ ምደባ ማስጠበቅ፣ የቡድኑን ዝግጁነት ማሻሻል እና ከክልሎች እና ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ትብብርን ማጠናከር ቀጣይ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መኾኑ ተመላክቷል።
ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ኢትዮጵያዊያን አይረሷትም፤ ስለፍቅር ሲሉም ቂም አይዙባትም”
Next articleበሰሜን ጎንደር ዞን በሰላም እጦት ምክንያት የተቋረጡ የፌዴራል መንገድ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት ምን እየተሠራ ነው?