
በደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ የተማሪዎች የትምህርት ተሳትፎን፣ የትምህርት ጥራትን እና ሥነ ምግባርን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሀብታሙ ጌታሁን ተማሪዎች በዕውቀት የዳበሩ እና በሥነ-ምግባር የተሻሉ እንዲኾኑ ባለድርሻ አካላት በትኩረት መሥራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።
የደብረ ታቦር ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ምክትል ኀላፊ አሠፋ ይስማው የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ የመምህራንን አቅም ማጎልበት እና ሥልጠና የመስጠት ተግባራት እየተከናወኑ መኾኑን ገልጸዋል። ተማሪዎች በሥነ-ምግባር የታነጹ እንዲኾኑ የግብረ ገብ ትምህርት በተለየ ሁኔታ እየተሰጣቸው ነው ብለዋል። የተማሪ ወላጆች ማኅበር በሚያከናውኗቸው ተግባራት የላቀ ውጤት ማስመዝገብ እንደተቻለም ገልጸዋል።
የተማሪ ወላጆች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዘላለም አለነ ወላጆች በትምህርት ቤቶች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል። ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ በገንዘብ፣ በቁሳቁስ እና ለተማሪዎች ጥናት ተስማሚ አካባቢ በመፍጠር የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች የትምህርት ቤቶችን የውስጥ ገቢ በማሳደግ የመማሪያ ክፍሎችን በመገንባት እና ገጽታቸውን በማሻሻል የተሻለ ሥራ ለማከናወን ትኩረት ሰጥተው እንደሚሠሩ አረጋግጠዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ደብረ_ታቦር #ጥቅምት_20_2019_ዓ_ም
👉 ዘጋቢ፦ ተክለብርሃን ፈንታ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
