
ባሕር ዳር የተፈጥሮ ጸጋዋን ከዘመናዊ መሠረተ ልማት እና አረንጓዴ ልማት ጋር በማቀናጀት ለነዋሪዎች ምቹ ከመኾን ባለፈ የዲፕሎማሲ፣ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ማዕከል እየኾነች ነው። የጣና ፎረምም ለዚህ ማሳያ ነው። ይህም ዘርፈ ብዙ ዕድሎችን አበርክቷል፤ ለቀጣይ መነሳሳትንም ፈጥሮላታል።
የጣና ፎረም ለከተማዋ የኢኮኖሚ እና የቱሪዝም ተጠቃሚነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የተናገሩት የከተማ አሥተዳደሩ ባሕል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት መምሪያ ኀላፊ ጋሻው እንዳለው ናቸው።
አሕጉር አቀፍ መድረኩ ለከተማዋ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ከማጎናጸፉም ባሻገር ከፍተኛ የቱሪዝም እንቅስቃሴ እንዲኖር አድርጓል። ይህንን አቅም ለማሳደግ የዲጂታል ቱሪዝም ሥራዎች፣ የሆቴል እና ሪዞርት ኢንቨስትመንቶች፣ ከተማዋን በፊልም እና በሚዲያ የማስተዋወቅ እንቅስቃሴዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል።
የፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች፣ ሌሎች አሕጉራዊ እና ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች በባሕር ዳር መካሄዳቸው ከተማዋ የኮንፈረንስ ብቻ ሳትኾን የታላላቅ ስፖርት ቱሪዝም ማዕከል እንድትኾንም አስችለዋታል ነው ያሉት።
የከተማዋን ቱሪዝም አጠናክሮ ለመቀጠል የምግብ፣ የማይስ እና የአድቬንቸር ቱሪዝም አማራጮችን በማስፋፋት ጎብኝዎች ረጅም ጊዜ እንዲቆዩ እና ተመልሰው እንዲመጡ እንደ ታንኳ፣ ሳይክል እና ሌሎችም አገልግሎቶችን ማሟላት እንደሚገባም ገልጸዋል።
#BahirDar #አሚኮ #TanaForum #Eco_Tourism
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_19_2019_ዓ_ም
✍️ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
