
በአማራ ክልል በበጀት ዓመቱ 129 የመስኖ ፕሮጄክቶችን ወደ ግንባታ ለማስገባት መታቀዱን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
የመስኖ እና ድሬንኤጅ ፕሮጄክቶች ግንባታ ክትትል ዳይሬክተር ጌትነት አያሌው ከተያዙት ፕሮጄክቶች ውስጥ 74ቱ ነባር ናቸው። 55ቱ ደግሞ በአዲስ ወደ ተግባር የሚገቡ ናቸው ብለዋል። የእነዚህ መካከለኛ እና አነስተኛ የመስኖ ፕሮጄክቶች የግንባታ የውል መጠናቸው14 ቢሊዮን ብር እንደኾነ ገልጸዋል።
48 የሚኾኑ ፕሮዴክቶች በፌዴራል ዘላቂ የልማት ስትራቴጅክ ግብ አማካኝነት የሚገነቡ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ በክልሉ የካፒታል በጀት እና 10 በሚኾኑ የተለያዩ የበጀት ምንጮች ወይም አጋር የልማት ድርጅቶች የሚገነቡ መኾናቸውን ጠቁመዋል።
የመስኖ ፕሮጄክቶቹ 21 ሺህ ሄክታር መሬት ለማልማት የሚያስችሉ ናቸው። ከ42 ሺህ በላይ የሚኾኑ አባውራ እና እማውራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ሥራ መገባቱን ነው የተናገሩት።
ከ129ኙ የመስኖ ፕሮጄክቶች መካከል 67ቱ በዚህ ዓመት እንደሚጠናቀቁ የተናገሩት ዳይሬክተሩ አሁን ላይ 13 የሚኾኑ ፕሮጀክቶች የግንባታ ሂደታቸው ተጀምሯል ነው ያሉት። በዝናብ እና በሰብል መሸፈን ምክንያት ወደ ሥራ ያልገቡ ፕሮጀክቶች መኖራቸውንም ጠቁመዋል።
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ጥቅምት_19_2019_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ ቴዎድሮስ ደሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
