ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያዩ።

12
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት አካሂጃለሁ ብለዋል።
ውይይታችን በኒውክሊየር ኃይል፣ በጤናና ንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር፣ በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሠረቱ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ ነበር ነው ያሉት።
በተጨማሪም፣ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ለኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ቀጣይነት ያለው እድገት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳየውን የመደመር መጽሐፌን የሩሲያኛ ዕትም ለፕሬዝዳንት ፑቲን አበርክቼላቸዋለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየክረምት በጎ ፍቃድን በማስቀጠል በበጋም ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል።