” ግጭት ሕዝብን የሚያጎሳቁል በመኾኑ ሰላምን መርጠናል” የሰላም አማራጭን የተቀበሉ ታጣቂዎች

6
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ በትጥቅ ትልግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ገብተዋል።
የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ወደ ጫካ በመግባታቸው ያገኙት መፍትሔ እንደሌለ ተናግረዋል።
ግጭቱ ሕዝቡን ከማጎሳቆል፣ ከወንድሞቻቸው ጋር ደም ከመቃባት፣ የሕዝብን ሃብት እና ንብረት ከማውደም በስተቀር ያተረፈው ነገር አንደሌለም ተናግረዋል። በፈጸሙት ተግባር መጸጸታቸውንም አንስተዋል።
ግጭትን በመቀጠል የሕዝቡን ሰላም ማረጋገጥ እንደማይቻል መገንዘባቸውን ተናግረዋል።
የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች ተቀናጅተው ክልሉን ለማውደም እየሠሩ መኾናቸውን የገለጹት ታጣቂዎቹ በዚህ ሁኔታ ውስጥ የሰላም አማራጭን መከተል ተገቢ መኾኑን ገልጸዋል።
በቀጣይም በአካባቢያቸው ሰላምን ለማስፈን፣ የልማት ሥራዎችን ለማፋጠን እና ለማኅበረሰቡ ዕድገት የራሳቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል።
ከምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በጫካ የሚገኙ ሌሎች ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየመገጭ ምርቃት የወለደው አዲሱ የቱሪዝም ብሥራት!
Next articleየሀገራችንን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የምናደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ዛሬ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል።