የአፍሪካ ከፍተኛ መሪዎች በጣና ፎረም ላይ ለመሳተፍ ባሕርዳር ከተማ እየገቡ ነው።

12
በሚኒስትር ማዕረግ የናሚቢያ የፕላን ሚኒስቴር ኮሚሽን ዳይሬክተር ጄኔራል ከይሪ ሙቤንዴን ጨምሮ የአፍሪካ ከፍተኛ መሪዎች፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የቀድሞ ታዋቂ የአፍሪካ ሰዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ጥናት እና ምርምር ላይ የሚሳተፉ ምሁራን ከዛሬ ጥቅምት 13/2019 ዓ.ም
ጀምሮ እስከ ጥቅምት 15/2019 ዓ.ም በባሕርዳር ከተማ የሚካሄደውን የጣና ፎረም ለመታደም ነው ባሕርዳር የገቡት።
የፎረሙ ተሳታፊ እንግዶች ባሕር ዳር ደጅአዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ
መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ፎረሙ ላለፉት 11 ዓመታት የተካሄደ ሲኾን ዘንድሮም ለ12ኛ ጊዜ በአፍሪካ ሰላም እና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ይጠበቃል።
✍️ ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleኢትዮጵያ ከመጀመሪያው ጀምሮ የጣና ፎረምን ዋና ባለቤት ኾና እያስተናገደች ቀጥላለች።
Next articleየአፍሪካውያን ውይይት፤ በጣና ዳሯ እመቤት