በባቲ ወረዳ እና በባቲ ከተማ የመከላከያ ሠራዊቱን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

9
በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በባቲ ወረዳ እና በባቲ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ ነዋሪዎች በነቂስ በመውጣት የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እንዲሁም ታሪካዊ ጠላቶችን እና ተልዕኮ ተሸካሚ የሀገር ውስጥ ባንዳዎችን የሚያወግዝ ሕዝባዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
በሰልፉ ላይ የሀገርን ሉዓላዊነት ማስከበር እና የሕግ ማስከበር ዘመቻውን የሚደግፉ፣ የሀገር አንድነትን እና የባሕር በር ጥያቄን የሚያጎሉ ልዩ ልዩ መፈክሮች ተስተጋብተዋል።
ይህ ሕዝባዊ ሰልፍ የሕዝብን ጠንካራ አንድነት፣ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ያለውን ደጋፊነት እና አብሮነት በሚያሳይ መልኩ በከፍተኛ ሀገራዊ ስሜት እና በታላቅ ድምቀት ነው የተካሄደው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleሀገር አፍራሾችን የሚያወግዝ፤ የሀገር መከታን የሚያወድስ ሕዝባዊ ሰልፍ በደጀን ወረዳ
Next articleበጎዛምን ወረዳ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።