በሞጃ እና ወደራ ወረዳ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

7
በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃ እና ወደራ ወረዳ የሀገር አፍራሽ የባንዳ እና የባዕዳን የጥፋት ድርጊትን የሚያወግዝ እንዲኹም የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።
በሰልፉ መልዕክት ያስተላለፉት የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላም እና ጸጥታ ምክትል ኀላፊ ዓባይ ድሌ መከላከያ ሠራዊት ለሀገሩ አንድነት እና ሉዓላዊነት ታላቅ ዋጋ እየከፈለ ሀገሩን የሚያጸና፣ መሥዋትነት በመክፈል በተግባር እያሳየ የሚገኝ የሕዝብ ልጅ ነው ብለዋል።
የወረዳው ዋና አሥተዳዳሪ የማነብርሃን ተስፋ የሰልፉ ዓላማ በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ የተሰነዘረውን የተቀናጀ የክህደት ጥፋት በጋራ ክንድ ለመቀልበስ እንደኾነም ጠቁመዋል።
እየተካሄደ ያለውን የሕግ ማስከበር ዘመቻ እና የሕልውና ትግል ሕዝቡ በአግባቡ ተረድቶ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመደገፍ ሀገራዊ ግዴታውን እንዲወጣም አሳስበዋል።
በሰልፉ ላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እየፈጸመ ላለው የሕግ ማስከበር ዘመቻ እና የሀገርን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ተግባር የሚደግፉ መልዕክቶች ተንጸባርቀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“የኢትዮጵያ አንድነት በጸረ-ሰላም ኃይሎች ሴራ አይደናቀፍም” የቡሬ ከተማ ነዋሪዎች
Next articleሀገር አፍራሾችን የሚያወግዝ፤ የሀገር መከታን የሚያወድስ ሕዝባዊ ሰልፍ በደጀን ወረዳ