
በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሀገር አፍራሾችን፣ የባንዳዎችን እና የባዕዳንን የጥፋት ድርጊት የሚያወግዝ እንዲሁም ለሀገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ዘብ ለቆመው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሙሉ ድጋፍ እና አጋርነትን የሚያረጋግጥ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል።
ከማለዳው ጀምሮ የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ እናቶች እና ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ወደ ዋና ዋና አደባባዮች በመውጣት ሀገራዊ አንድነትን እና ለሠራዊቱ ያላቸውን ደጀንነት የሚያንፀባርቁ መፈክሮችን በማስተጋባት አቋማቸውን እየገለጹ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
