ሰባት ነገሮች ስለጣና ፎረም፦

3
ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም (አሚኮ) ✍️እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2012 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሰላምና ደህንነት ኢንስቲትዮት ሃሳብ አመንጭነት ተመሰረተ።
✍️ዋና ዓላማዊ ለአፍሪካው የሰላምና ደህንነት ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ ማበጀት ነው።
✍️ዓመታዊ መድረክ ሲኾን በጣናዋ ንግስት ባሕር ዳር ከተማ በየዓመቱ ይደረጋል።
✍️ከተለያዩ ዓለማት የተወጣጡ ከ250 የሚበልጡ ተሳታፊዎች ይታደማሉ።
✍️የቀድሞ የሀገራት መሪዎች፣ ፖሊሲ አዎጭዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የማኅበረሰብ ተወካዮች፣ ወጣት መሪዎች፣ የደህንነት ሰዎች፣ ዓለም አቀፍ አጋሮች ይገኙበታል።
✍️ዘንድሮም ከጥቅምት 13-15/2019 ዓ.ም በባሕር ዳር ይደረጋል።
✍️በሰላም ግንባታ፣ በብሔራዊ ደህንነት፣ ቀጣይነት ባለው እድገት እና በተጨባጭ የግጭት መፍቻ መንገዶች ዙሪያ ውይይት ተደርጎ አፍሪካዊ መፍትሄ እንደሚፈለግ ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleቡና እና የልብ ጤና ከጥናቶች፦
Next article“ስለ ኢትዮጵያ ጸንተዋል፤ ጠላቶቿንም አሳፍረዋል”