ቡና እና የልብ ጤና ከጥናቶች፦

4
ባሕር ዳር: ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም (አሚኮ) ይህ ጥያቄ የብዙ ሰዎችን ቀልብ ሲስብ የቆየ አከራካሪ ርዕስ ነው። ቡና አነቃቂ የካፌይን ይዘት አለው። በልብ ምት፣ በደም ግፊት እና በደም ቧንቧዎች ላይ የሚፈጥረው ተጽዕኖ በሳይንስ ሊቃውንት ዘንድ ትኩረት ተሰጥቶት ሲጠና ቆይቷል።
​በዚህ ጉዳይ ላይ የአሜሪካ የልብ ሕሙማን ማኅበር (American Heart Association – AHA) በታዋቂው Circulation ሳይንሳዊ መጽሔት ላይ አዲስ የምርምር መረጃ አውጥቷል። መረጃው የካፌይን እና የቡና አጠቃቀም በልብ እና ደም ቧንቧ ጤና ላይ የሚያደርሰውን ተጽዕኖ በዝርዝር ፈትሾታል።
​ጥናቱ እንደሚያመላክተው ቡናን በተገቢው መጠን መጠጣት ለአብዛኞቹ አዋቂዎች ምንም ዓይነት የልብ ሕመም ሥጋት አያመጣም። ተፈጥሮአዊ ይዘቱን ጠብቆ ከተወሰደ ደግሞ በርካታ የጤና ጥቅሞችን ይሰጣል።
​ከጥቅሞቹ መካከልም፦
​#የስኳር በሽታ ሥጋትን ይቀንሳል፦
ያለ ምንም ማጣፈጫ አዘውትሮ ቡና መጠጣት ለዓይነት 2 የስኳር በሽታ የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል።
​
#የልብ ሕመም፣ የስትሮክ እና የልብ ድካም አደጋን ይከላከላል፣ በቀን ከ2 እስከ 4 ሲኒ ጥቁር ቡና መጠጣት ከእነዚህ ከባድ የልብ እና ደም ቧንቧ ሕመሞችን ይከላከላል።
#የሰውነት መቆጣትን እና ኦክሲዴሽንን ይከላከላል። ቡና ከካፌይን ባሻገር ለሰውነት ጤና ጠቃሚ የኾኑ በርካታ የተፈጥሮ አንቲኦክሲዳንት ንጥረ ነገሮችን ይዟል።
#አንጎልን ያነቃል፤ ትኩረትንም ይጨምራል። በቡና ውስጥ ያለው ካፌይን በአጭር ጊዜ ውስጥ የአንጎል ንቃተ ህሊናን በማንሳት ንቁ ያደርጋል።
✍️ቡናን በሚጠጡበት ጊዜ ሊደረጉ የሚገቡ ጥንቃቄዎች፦
​#የመጠኑ ወሰን መከበር አለበት። በቀን እስከ 400 ሚሊግራም ካፌይን) ባለው መጠን ብቻ መጠጣት አለበት፣
​# ቡናን ያለ ማጣፈጫ መጠጣት፦ የቡናው ተፈጥሮአዊ ጥቅም እንዳይጠፋ ያለ ምንም ስኳር፣ ፍሌቨር ወይም ተጨማሪ ቅባት መጠጣት አለበት፣
​#የአፈላል ዘዴው በጥንቃቄ መመረጥ አለበት፦ ኮሌስትሮል እንዳይጨመር በሚፈላበት ጊዜ በወረቀት ማጣሪያ (paper filter) የተጣራ ቡና መጠጣት አለበት።
​#የልብ ደም የመረጨት አቅም እንዳይቀንስ እና የልብ ምት እንዳይዛባ በቀን ከ4 ሲኒ በላይ አለመጠጣት አለበት።
​#የሰውነት ምላሽ በጥንቃቄ መታየት አለበት፦ የካፌይን ተጽዕኖ እንደ ዘረመል፣ ሜታቦሊዝም እና ዕድሜ ስለሚለያይ እያንዳንዱ ሰው የራሱን የሰውነት ኹኔታ መከታተል አለበት።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleከጉባ እስከ ቀይ ባሕር የተዘረጋውን የተንኮል መረብ የሚበጣጥሰው የቀጣናው ጠንካራ ኀይል።
Next articleሰባት ነገሮች ስለጣና ፎረም፦