
አባት አርበኛ መለሰ ግርማይ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ ሲኾኑ በወታደራዊ ወኔ፣ በቀረርቶ እና በፉከራቸው የታወቁ ታዋቂ ሀገር ወዳድ ናቸው።
በወጣትነት ዕድሜያቸው የጀግናው ሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል በመኾን ለ10 ዓመታት ሀገራቸውን ያገለገሉ ሲኾን በአሁኑ ወቅትም የአባት አርበኞች አባል በመኾን የአካባቢያቸውን ሰላም እና ጸጥታ በማስጠበቅ ላይ ይገኛሉ።
“የሀገር መከላከያ ሠራዊት ማለት ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጣ የኅብረ-ብሔራዊነታችን ማሳያ እና መገለጫ ነው” ይላሉ።
“የዚህ ታላቅ ሠራዊት አባል ኾኜ ማገልገሌ ትልቅ ደስታ እና ኩራት ይሰማኛል፤ ሠራዊቱን መደገፍ ደግሞ የሁላችንም ሀገራዊ አደራ ነው” ሲሉ ገልጸዋል።
አባት አርበኛ መለሰ ግርማይ ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን አክብሮት እና ፍቅር ንም በግጥም አቅርበዋል።
መከላከያ የሀገር አርማችን፣
ሕይወት ገብሮ ለሰላማችን።
መትረየስ ሲጮህ ድሽቃው ሲያጓራ፣
መድፉ ቢተኮስ ቢጨስ አቧራ፤
በየገባበት የማይደነግጥ፣
ከተጠመደ እጁን የማይሰጥ፤
ኢትዮጵያን ብሎ የተማማለው፣
ሀገሬን ብሎ የተማማለው፤
አይመለስም ሳይደርስ ካሰበው! ሲሉም ተቀኝተዋል
#የመደመር_መንግሥት!
#ትልቅ_ሀገር_ትልቅ_ሕዝብ_ታላቅ_ርዕይ!🇪🇹
#ሰቆጣ #ጥቅምት_07_2019_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
