“ባሕር ዳር የከተማ ውበትን ከመደመር መንግሥት የሥልጣኔ ግብ ጋር አስተሳስራ የዘመናዊት ኢትዮጵያን አዲስ ገጽታ እያንፀባረቀች ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

10
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት ፕሮጄክትን አስጀምረዋል። በግንባታ ማስጀመሪያው ላይ እንደገለጹት ባሕር ዳር የከተማ ውበትን ከመደመር መንግሥት የሥልጣኔ ግብ ጋር አስተሳስራ የዘመናዊት ኢትዮጵያን አዲስ ገጽታ እያንፀባረቀች ነው ብለዋል።
ዛሬ የክልሉን ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት እና ቤተመንግሥት ግንባታ አስጀምረናል፤ ጣና እና ዓባይ በሚታዩበት የጣና ማዕዘን ላይ የሚገነባው ግንባታ ላይ በቦታ መረጣ እና በተሻለ ዲዛይን እንዲገነባ ሐሳብ የሰጡን የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ አብርክቷቸው ልዩ በመሆኑ ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉም ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ የመደመር መንግሥት የሥራ ከባቢን ከማሻሻልና ደረጃቸውን የጠበቁ ጠንካራ ተቋማትን የመገንባት ርዕይን ማዕከል ያደረገ መኾኑንም ተናግረዋል።
የርዕሰ መስተዳደር ጽሕፈት ቤት እና ቤተመንግሥቱ ከክልሉ እሴቶችና መለያ ባህሪያት በመነሳት በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የተነደፈ ሲኾን፣ ዘመናዊነትን ከሀገር በቀል እሳቤ ጋር ያጣመረ ነው ብለዋል።
የመንግሥት ተቋማትን ማዘመን ለተሻለ አስተዳደርና ለሕዝብ የተሻለ አገልግሎት ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ሲሉም መልእክት አስተላልፈዋል።
Previous articleጣና ፎረም – የባሕር ዳር ውበት መታያ አንዱ በር!
Next article“ዛሬ የተጀመረው ፕሮጄክት ዘመን የሚሻገር፤ የአማራ ክልልን ሕዝብ ባሕልና ታሪክም የሚገልጽ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ