ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ

2
ለሰላም ቅድሚያ ሰጥቶ መሥራት፤ ቃልን በተግባር ማሳየት፤ ከአዲሱ መንግሥት የሚጠበቅ የቤት ሥራ ! ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ የመንግሥት ምስረታ እየተከናወነ ይገኛል።
ይህንን የመንግሥት ምስረታ በተመለከተ አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡት የቡሬ ከተማ ነዋሪዎች መንግሥት ቃል የገባቸውን ሥራዎች በተጨባጭ በሥራ ማረጋገጥ ይኖርበታል ብለዋል።
የሁሉ ነገር መሠረት የኾነውን የሰላም ሁኔታ ማረጋጋት እና የሕዝቡን በሰላም ወጥቶ የመግባት ሁኔታ ማስጠበቅ ላይ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲሠራም ጠቁመዋል።
በተለይ የሕዝቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ በጉባ ላይ የተበሰሩ የማዳበሪያ ፋብሪካ፣ የነዳጅ ማጣሪያ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ማከናወን ላይ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋልም ነው ያሉት።
በወረዳ፣ በክልል እና በፌዴራል ደረጃ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ከአዲሱ መንግሥት የሚጠበቅ የቤት ሥራ ነውም ብለዋል።
በትልልቅ ከተሞች የተጀመረው ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ሥራ ታች ድረስ በማውረድ ለኅብረተሰቡ የልማት ተጠቃሚነት ሊተጋ እንደሚገባም ጠይቀዋል።
በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን እና ሕዝብን ለምሬት የሚዳርጉ ጉዳዮችን ለማሻሻል ሰፊ ሥራ መሥራት እንዳለበት ነው ነዋሪዎች የገለጹት።
ለዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፈት ይገባል ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ንጉስ ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!
Next articleለጥንቃቄ፦