ማኅበራዊ ሚዲያን ከልክ በላይ ሲጠቀሙ ጤናዎት ላይ ምን እንደሚፈጠር ያውቃሉ?

13
ባሕር ዳር፡ መስከረም 19/2019 ዓ.ም (አሚኮ) ከእንቅልፋችን ስንነቃ ከምንፈልጋቸው የመጀመሪያ ነገሮች አንዱ የእጅ ስልካችን ከኾነ ሰነበተ፡፡ማኅበራዊ ሚዲያ ከዓለም ጋር የሚያገናኝ እና እውቀት የምንቀስምበት ድንቅ መሣሪያም ነው።
ነገር ግን አጠቃቀሙ ከወሰን ሲያልፍ በአዕምሮ፣ በሥነ-ልቦና እና በአካል ላይ የጤና አደጋ ያስከትላል።
✍️ከልክ በላይ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ማሳለፍ የሚያመጣቸው የጤና ችግሮች፦
#የአዕምሮ ጤና እና ሱስ፦ «ላይክ» እና ማሳወቂያዎች (Notifications) በአዕምሮ ውስጥ ዶፓሚን በመልቀቅ ከቁማር ጋር የሚመሳሰል ሱስ ያስከትላሉ፡፡
#የድብርት እና ጭንቀት መጨመር፦ በቀን ከሦስት ሰዓት በላይ ስልክ የሚጠቀሙ ታዳጊዎች ለድብርትና ጭንቀት የመጋለጥ ዕድላቸው በእጥፍ ይጨምራል፡፡
#የእንቅልፍ መዛባት፦ በምሽት ከስክሪን የሚወጣው ሰማያዊ ብርሃን (Blue Light) የእንቅልፍ ሆርሞን (Melatonin) ምርትን በመግታት ለተለያዩ በሽታዎች ያጋልጣል፡፡
#የራስን ዕሴት ማጣት፦ በጉርምስና ዕድሜ ላይ ያሉ ወጣቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ንጽጽር ሳቢያ የብቸኝነት እና የበታችነት ስሜት ይፈታተናቸዋል።
✍️መፍትሔዎቹ፦
#የጊዜ ገደብ ማበጀት፦ በቀን ከ30 እስከ 60 ደቂቃ ብቻ መጠቀም፤
#ስክሪን አልባ ቀጣናዎች፦ መኝታ ቤት እና የመመገቢያ ጠረጴዛ ላይ ስልክ አለመጠቀም (ከመተኛት 1-2 ሰዓት በፊት ስክሪን መተው)፤
#የዲጂታል እረፍት (Digital Detox)፦በሳምንት ወይም በወር የተወሰኑ ቀናትን ከማህበራዊ ሚዲያ ሙሉ በሙሉ መራቅ፤
#ማሳወቂያዎችን ማጥፋት እና ገጾችን ማጣራት፦ አላስፈላጊ ማሳወቂያዎችን (notfications) በመዝጋት አዕምሮን ከሚረብሹ ገጾች መራቅ፤
#አካላዊ እንቅስቃሴ እና ንባብ፦ ጊዜን በስፖርት፣ በመጻሕፍት ንባብ እና ከቤተሰብ ጋር ባለው የፊት ለፊት ግንኙነት መተካት ይገባል።
ምንጭ፦ በኲር
ሙሉን ዘገባውን ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ ይከፈቱ!
👇
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article” የቀጣናው የሰላም ዘብ”
Next articleበአረንጓዴ አሻራ የጎመራው የንብ ማነብ ልማት