በሰከላ ወረዳ ዙሪያ የተሰማራው ጥምር ጦር ግዳጁን በብቃት እየተወጣ ነው።

6

 

በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ ከሚገኙ የጥምር ጦር መሪዎች ጋር የአካባቢውን የሰላም ሁኔታ በተመለከተ ውይይት ተካሂዷል።

በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ጀማል አማን በወረዳው ተሰማርቶ ግዳጁን በብቃት እየተወጣ የሚገኘው ጥምር ጦር ማንኛውንም ግዳጅ መወጣት በሚችልበት አስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።

የጥምር ጦሩ የማድረግ አቅም ከመቸውም ጊዜ በላይ በጥንካሬ ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

የሰከላ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ዓለማየሁ አዳነ ወረዳው አሁን ለሚገኝበት አንጻራዊ ሰላም ከሠራዊቱ በተጨማሪ የሰላም አስከባሪው እና የሚሊሻው ሚና የላቀ እንደነበር ገልጸዋል። የጥምር ጦሩ ግዳጅ የመፈጸም ብቃት አበረታች ነውም ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊ መሪዎች በሰጡት አስተያየት የጥምር ጦሩ ወታደራዊ ቁመና እና የሥነ ልቦና ዝግጁነት የሚደነቅ መኾኑን ገልጸዋል። የሕዝባዊነት ባሕሪውን በመላበስ በመልካም ቁመና ላይ መኾኑንም ተናግረዋል። መረጃው የምሥራቅ እዝ ነው።

#አሚኮ #ሰላም #ኢትዮጵያ 🇪🇹

#ባሕር_ዳር #መስከረም_09_2019_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ለዘላቂ ሰላም ሴቶች የእናትነት ጥበባቸውን መጠቀም አለባቸው” እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር)