
ግዙፉ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ከ5 ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ሊያስተናግድ ነው።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ2019 የውድድር ዘመን የዕጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት መከናወኑን ተከትሎ የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከአምስት ዓመታት በኋላ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን እና ደጋፊዎችን ለመቀበል ተዘጋጅቷል።
ጥቅምት 13 በአራተኛ ሳምንት ጨዋታ ባሕር ዳር ከተማ ከአምስት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በገዛ ሜዳው ከደጋፊዎቹ ፊት ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር ይጫወታል።
ጥቅምት 20 በአምሥተኛ ሳምንት ደግሞ የአማራ ክልል ተወካዮቹ ፋሲል ከነማ እና ባሕር ዳር ከተማ የሚያደርጉት ጨዋታ ለስታዲየሙ ሌላ ሞገስ እንደሚኾን ይጠበቃል።
ይህ ጨዋታ ላለፉት ዓመታት ኳስ ሲናፍቅ ለቆየው የባሕርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ደጋፊ ትልቅ ዕድል በመኾኑ ዕለቱ በጉጉት ነው የሚጠበቀው።
#አሚኮ #ስፖርት🇪🇹
#ባሕር_ዳር #መስከረም_07_2019_ዓ_ም
በሐናማርያም መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
