🛺 “የዕለት ጉርሱን ሸጦ ለከተማው ክብር የገዛው የደሴው ብርቱ ወጣት!

10

‎
‎ከክሊኒካል ነርሲንግ እስከ ደን እና አረንጓዴ ልማት ባለሙያነት አገልግሏል። አሚኮ እና አልማ በትብብር በሚያዘጋጁት ብቁ ወጣት የሥራ ፈጣሪነት ውድድር ላይ ያገኘነው የደሴ ከተማ ነዋሪው ወጣት ደሳለኝ ካሳ አሁን ላይ ከአካባቢ የሚሰበሰቡ ደረቅ ቆሻሻዎችን መልሶ በመጠቀም አስደናቂ ቁሳቁሶችን እያመረተ ይገኛል።
‎
‎ወጣት ደሳለኝ ቆሻሻዎችን ከመኖሪያ ቤቶች፤ ከመንግሥት እና ከግል ድርጅቶች እንዲሁም ከሕክምና ማዕከላት በመሰብሰብ አጽድቶ፣ ፈጭቶ እና ኬሚካል ጨምሮ ለጥሬ ዕቃነት ያዘጋጃቸዋል። በመቀጠልም እንደ የሚፈጩ እና እና በአንድ ላይ የሚጨፈልቁ መሣሪያዎችን በመጠቀም ለጠንካራነታቸው ዋስትና የሚሰጣቸውን የሲኒ ማቅረቢያዎች፤ የፈርኒቸር ውጤቶች፤ የአበባ ማስቀመጫዎች፤ የማስታወቂያ ፊደላት እና ሎጎዎችን ያመርታል።
‎
‎የሥራው ዋነኛ መነሻ እና ጥቅሞች፦

‎በየቦታው የሚጣሉ እና አፈርን የሚበክሉ ቁሳቁስ በመቀነስ ንጹሕ እና ውብ ከተማ ለመፍጠር የሚያስችል ድንቅ ሥራ እንደኾነ የፈጠራ ባለቤቱ ይናገራል።
‎
‎ከፋይበር ግላስ፣ ሲሚንቶ እና ማይካ ጋር ሲነጻጸር በቀላሉ የማይሰበር፣ ቢሰበር እንኳ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚደረግ ወይም የሚጠገን መኾኑንም ነው የተናገረው።
‎
‎ወደፊት የፈርኒቸር ውጤቶችን ሙሉ በሙሉ በመተካት የእንጨት ፍላጎትን ይቀንሳል። ይህ ደግሞ የደን ጭፍጨፋን ማስቀረት ይችላልም ብሏል።
‎
‎ወጣት ደሳለኝ ይህንን ትልቅ ህልም በተግባር ያዋለው ይሠራባት የነበረውን ባጃጅ ሸጦ መነሻ ገንዘብ በመያዝ አንደኾነም ገልጿል። አሁን ላይ የማምረቻ እና የቆሻሻ ማከማቻ ቦታ እጥረት እንዳለበት ጠቁሟል።
‎
ግለሰቡ በአልማ የብቁ ወጣት ውድድር ላይ ከዳኞች ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል! 👏

#አሚኮ #innovation #ኢትዮጵያ🇪🇹
‎
‎#ባሕር_ዳር #መስከረም_06_2019_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
‎

Previous articleሰብልን ከአንበጣ እና ግሪሳ ወፍ እንዴት መከላከል ይቻላል?