“ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

14

 

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጳጉሜን 04 የሚከበረውን የኅብር ቀን አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል። የመልእክቱ ሙሉ ይዘት እንደሚከተለው ቀርቧል።

የኅብር ቀን
ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች!

በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል። ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ ድረስ፤ ሁላችንም በአንድነት ስንቆም የጋራ ትርክቶቻችን ወደ ጋራ ስኬት እንደሚያሻግሩን በተግባር አሳይተናል።
እኛ የምንገነባው አካታች የሆነች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች፣ የአብሮነትና መረዳዳት ባህል የጎለበተባት ጠንካራ ሀገር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጋራ ታላቅነትና እምቅ አቅም በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን። በአንድነት ወደ ብልጽግና ጉዟችን እንቀጥላለን።

አንድ ሕዝብ፣ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ!

#አሚኮ #EthiopiaPrevails #Ethiopia

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleኢትዮጵያ እና ጽናት የማይነጣጠሉ ናቸው
Next articleኢትዮጵያ የብዝኃ ማንነቶች ድምር ናት፡፡