
የ25 ዓመት አሻጋሪ እና ዘላቂ የልማት ዕቅድ ታቅዶ ወደ ሥራ የተገባበት የመጀመሪያው ዓመት በግብርና ዘርፎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታውቋል።
የቢሮው ኀላፊ ደረጀ ማንደፍሮ በክልሉ ከተመዘገበው የ7 ነጥብ 9 በመቶ ጥቅል የምርት ዕድገት ውስጥ የግብርና ዘርፉ ሚና ከ5 ነጥብ 5 በመቶ በላይ መኾኑን ገልጸዋል።
በምርት ዘመኑ የአፈር ማዳበሪያ እና የምርጥ ዘር አጠቃቀም፤ ክላስተርን መሠረት ያደረጉ የሰብል ምርት ሥራዎች እና ሌሎች ለሰብል ምርት እድገቱ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል ነው ያሉት።
ቢሮ ኀላፊው በ2017/18 የምርት ዘመን ከ188 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሠብሠቡንም አውስተዋል።
የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት፤ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር፤ የግብርና ሜካናይዜሽን አቅርቦት፤ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት በምግብ ራስን የመቻል ዘመቻ እና ሌሎች ኢኒሸቲቮች ትልቅ አፈጻጸም ተመዝግቦባቸዋል ብለዋል።
ከሜካናይዜሽን አቅርቦት አኳያ በበጀት ዓመቱ 978 በላይ ትራክተር መሠራጨቱን ተናግረዋል። በምግብ ራስን ለመቻል በተደረገው ጥረትም ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን የጠቀሱት ኀላፊው የሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ ወረዳ ከተረጅነት ሙሉ በሙሉ መውጣቱን እውቅና ሰጥተዋል። ሌሎች ተሞክሮ ሊወስዱበት እንደሚገባም አንስተዋል።
በ2019 የምርት ዘመን ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች፦
ዘጋቢ፦ አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
