“ዘላቂ ሰላምን ለመገንባት በተቋማት መካከል የሚደረግ የተቀናጀ አሠራር እና ጠንካራ ትብብር ወሳኝ ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

23
በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ በሌተናል ጀኔራል አስራት ዴኔሮ የተመራ የከፍተኛ መሪዎች ቡድን በሁለተኛ ቀን የባሕር ዳር ቆይታው በከተማ አሥተዳደሩ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅት የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በስፍራው ተገኝተው ለአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አስራት ደኔሮ እና ለልዑካን ቡድኑ የክብር ማስታወሻ ስጦታ አበርክተዋል።
ርዕሰ መሥተዳድሩ ባስተላለፉት መልእክት የሁለቱ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያዎች ግንኙነትና ትብብር የሕዝብን ሰላም እና ደህንነት ከማስጠበቅ ባለፈ የልማት ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።
“የክልሉን እና የሀገሪቱን ሰላምና ጸጥታ በዘላቂነት ለማስከበር በተቋማት መካከል የሚደረግ የተቀናጀ አሠራር እና ጠንካራ ትብብር ወሳኝ ነው!!” ሲሉ ርእሰ መሥተዳድሩ ገልጸዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ እና በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ ልምድ እና መረጃ በመለዋወጥ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ጠቁመዋል።
ይህን ወንድማማችነታዊና ሙያዊ ትስስር አጠናክሮ ማስቀጠል የሕዝብን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ መሆኑንም አስገንዝበዋል።
ይህ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች ጉብኝት በሁለቱ የፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያዎች መካከል ያለውን የሙያና የቴክኖሎጂ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክርና ለወደፊት የጋራ ሕግ ማስከበር ሥራዎች ትልቅ መሰረት የሚጥል መሆኑ ተመልክቷል።
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleልጃቸውን በግል ትምህርት ቤት ያስተማሩት አርሶ አደር- የከፍተኛ ውጤት ባለቤቱ ተመሥገን ወላጅ አባት ሉሌ ተኮላ አቶ ሉሌ ተኮላ የትውልድ ግንባታ ተጋድሎ ሕያው ምስክር ኾነው ብቅ ብለዋል።
Next articleየሰውነት ማጎልበት ስፖርተኞች በተለየ በልብ ህመም ለምን ይጠቃሉ?