ከመሬት ሥር የተደበቀው ቢሊዮን ዶላር በአማራ ክልል

23
​የአማራ ክልል ከፍተኛ የማዕድን ክምችት የሚገኝበት አካባቢ ነው። ወርቅ፣ ኦፓል፣ የድንጋይ ከሰል፣ እምነበረድ፣ ብረት፣ ግራናይት፣ ጋብሮ እና ሌሎችም ከ50 በላይ ማዕድናት በክልሉ መኖራቸው በጥናት የተረጋገጠ ነው።
የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ ኃይሌ አበበ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት በክልሉ ለማዕድን ክምችት መሠረት የሆኑት ሦስቱም የአለት አይነቶች በስፋት ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት የማዕድን ዘርፉ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለመዋቅራዊ ሽግግር መሠረታዊ መኾኑ ታምኖበት ከዋና ዋና የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ ኾኖ በትኩረት እየተሠራበት ነው ብለዋል።
​ማዕድን ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት እና የመንግሥትን ገቢ ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አብራርተዋል። በዚህም ከዘርፉ ተጠቃሚ ለመኾን የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ነው ያሉት።
📌በክልሉ የማዕድን ጸጋዎች ፍለጋ ምን ላይ ነው?
ከክልሉ መንግሥት የ2018 በጀት ዓመት ሪፖርት የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በበጀት ዓመቱ:-
✍️ በ20 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት መሬት ላይ በተካሄደው የላብራቶሪ ጥናት ከ146 ነጥብ 7 ሜትሪክ ቶን በላይ ብረት ተገኝቷል።
✍️ በ10 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት በተደረገ ጥናት ከ5 ነጥብ 1ሚሊዮን ቶን በላይ የብረት ማዕድን ክምችት ማግኘት ተችሏል።
✍️በ440 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ የኮንስትራክሽን ማዕድናት ፍለጋ ጥናቶች ተሠርተው 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ቶን ግራናይት እና ከ1ነጥብ 6 ቢሊዮን ቶን በላይ ጥቁር ድንጋይ ማግኘት ተችሏል።
✍️ከ6 ነጥብ 4 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ኖራ ለማምረት የሚያስችል የኖራ ማዕድን የክምችት ቦታዎች በጥናት ተለይተዋል።
📌ከማዕድን ሃብት የተገኘ ገቢ
ቢሮ ኀላፊው እንዳብራሩት:-
💎 ጥሬ ኦፓል:- በበጀት ዓመቱ 27 ሺህ 127 ኪሎ ግራም ጥሬ ኦፓል ለገበያ ቀርቧል። ከዚህም 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።
🔹የተዋበ ኦፓል:-729 ኪሎ ግራም እሴት የተጨመረበት የተዋበ ኦፓል ለገበያ በማቅረብ 1 ነጥብ4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል።💎
🔹ወርቅ:- 357 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ በማቅረብ 61 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል።🪙
🔹ድንጋይ ከሰል፣ ጂፕሰም እና ግራናይት የመሣሠሉ ምርቶችን በክልሉ በማምረት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ተችሏል።
🔹በዘርፉ በበጀት ዓመቱ ከ55 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል።
🔹 በተለያዩ የገቢ አማራጮች ከ346 ሚሊዮን ብር በላይ ለክልሉ ገቢ ማስገኘቱን በአብነት አንስተዋል።
🔹 ይህንን ከመሬት ስር የተደበቀውን የቢሊዮን ዶላር ጸጋ በአግባቡ መጠቀም ጊዜው አሁን ነው በሚል እሳቤ የክልሉ መንግሥት በአሻጋሪ የዕድገት እና የልማት ዕቅዱ አካትቶ በመሥራት ላይ ይገኛል።
✅​ የክልሉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ስልጠናን ማጠናከር ፣ የስነ-ምድር ካርታ ዝግጅት ማስፋፋት፣ የፋይናንስ አቅርቦትን ማመቻቸት፣ የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና ሕጋዊነት የማስፈን ሥራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሠራ መሆኑን ቢሮ ኀላፊው አመላክተዋል።
💭 እርስዎስ ይህንን የማዕድን ሃብት ጥቅም ላይ ለማዋል ምን መደረግ አለበት ይላሉ? አስተያየትዎን ያጋሩ፡ 👇
✍️ ​በአሰፋ ልጥገበው
Previous articleለዓመታት ሞትን፤ ታገትን፤ በአዲሱ ዓመት ሰላምን ስጡን!