
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት 84 ተማሪዎችን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አስፈትኗል። ከእነዚህ ውስጥ 80 ተማሪዎች ከ500 በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል።
ባለፈው ዓመት ካስፈተናቸው ተማሪዎች 80 ከመቶ ከ500 በላይ ማምጣታቸውን የገለጹት የትምህርት ቤቱ ርእሰ መምህር ሳሊም አህመድ የዘንድሮው ከባለፈው መሻሻሉን አስረድተዋል።
ሦሥት ተማሪዎች ብቻ ከ450 እስከ 499 ውጤት አስመዝግበዋል ነው ያሉት።
በትምህርት ቤቱ በወንዶች 587 ነጥብ 1 እና በሴቶች 570 ነጥብ 5 ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧልም ብለዋል።
የማጠናከሪያ ትምህርት በተጠናከረ መልኩ መሰጠቱ፣ ተማሪዎች እርስ በእርስ እየተረዳዱ እንዲያጠኑ መደረጉ ለተማሪዎች ውጤት መሻሻል በምክንያትነት ተጠቅሷል።
የይሁኔ ወልዱ መታሰቢያ ደሴ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት በ2019 የትምህርት ዘመን ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ከ400 በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑን ጠቁመዋል።
ዘጋቢ፦ ከድር አሊ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
