በአዲስ አበባ ዘመናዊ ተርሚናሎች በመገንባታቸው የትራፊክ አደጋን 25 በመቶ ቀንሷል።

10
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ዋና ዳይሬክተር ክበበው ሚዴቅሳ የተቀናጁ ተርሚናሎች የሕዝብ ትራንስፖርት መዳረሻዎችን እና ፕላዛዎችን ለማስፋፋት ብቻ የሚያገለግሉ አይደሉም ብለዋል።
የመንገድ ላይ የተሽከርካሪ ጫናን በመቀነስ እና የከተማዋን የትራፊክ ፍሰት በማሳለጥ ረገድም ጉልህ ሚና አላቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ተቋሙ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመተባበር የተገልጋዮችን እንግልት ለመቀነስ እና የትራፊክ አሥተዳደሩን ለማሻሻል እየሠራ መኾኑንም ገልጸዋል።
አዳዲሶቹ የትራንስፖርት ተርሚናሎች እና ተያያዥ ልማቶች በከተማዋ ለዘመናት የቆዩ የመኪና ማቆሚያ እና የትራፊክ ችግሮችን ለመቅረፍ እያገዙ መኾናቸውም ተጠቁሟል።
በአዲስ አበባ በተገነቡ ዘመናዊ ተርሚናሎች እና ተያያዥ ልማቶች የትራፊክ አደጋ በ25 በመቶ መቀነሱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ቢሮ ገልጿል።
ፕሮጀክቶቹ ከ1 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ዜጎችም የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ነው የተጠቆመው።
በአራቱ ተርሚናሎች የተገነቡ የፓርኪንግ ስፍራዎች ቀበና 122፣ የካ 49፣ ቦሌ 81 እና ጎተራ 252 መኾናቸው ተገልጿል።
በአጠቃላይ አዳዲሶቹ ዘመናዊ ተርሚናሎች የሕዝብ ትራንስፖርትን በተቀናጀ ሥርዓት ለማሥተዳደር፣ የትራፊክ መጨናነቅን እና የመንገድ ዳር ጫናን ለመቀነስ እንዲኹም ለነዋሪዎች ምቹ እና ዘመናዊ የከተማ አካባቢ ለመፍጠር የሚያግዙ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበ2019 ዓ.ም በአማራ ክልል በትምህርት ዙሪያ ምን ታስቧል?