መውሊድ የመረዳዳት እና የፍቅር በዓል

3
1 ሺህ 501ኛው የነብዩ መሐመድ ( ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በጎንደር ከተማ አሥተዳደር
በጀሚአልከበሪ መስጊድ እየተከበረ ነው።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ሐሰን ደሴ (ዶ.ር) የከተማ አሥተዳደሩ የክርስቲያን እና የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አብሮ የመኖር የዘመናት ታሪክ ያለው መኾኑን ተናግረዋል።
የፍቅር፣ የሰላም እና የመከባበር መገለጫ የኾነው የመውሊድ በዓል ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዓሉ ሲከበር እርስበርስ በመረዳዳት፣ የነብዩን አስተምህሮ በተግባር በማሳየት መኾን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ሠብሣቢ ኢብራሒም መሐመድ የነብዩን አስተምህሮ በመከተል እና በመተግበር በዓሉን ማሳለፈ እንደሚገባ ገልጸዋል።
ነብዩ መሐመድ ( ሰ.ዐ.ወ) ለዓለማት ዕዝነት ተብለው የተላኩ ነብይ መኾናቸውን ታሳቢ በማድረግ የተቸገሩትን በመርዳት እያከበሩ እንደኾነ የበዓሉ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ዘጋቢ፦ ማርታ አዱኛ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleለነብዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የእናትነት ፍቅር የለገሱት ኢትዮጵያዊት እናት።
Next articleሰላም እና አንድነት የሚሰበክበት የመውሊድ በዓል