“በጤናው ዘርፍ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓል” ዶክተር መቅደስ ዳባ

7
የጤና ሚኒስቴር እና የክልል ጤና ቢሮዎች የጋራ የውይይት መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ እንደተናገሩት የጋራ መድረኩ በአማራ ክልል መደረጉ የክልሉ የጤና ዘርፍ እንዲነቃቃ፤ መበረታታትን እና መደጋገፉ እንዲኖር የሚያደርግ ነው።
በክልሉ የጤና ሥርዓቱን ለማሻሻል ከጤና ኬላ እስከ ጤና ቢሮ ድረስ አሠራሮችን የማዘመን ሥራ መሠራቱንም አንስተዋል።
በማኅበረሰብ ዓቀፍ የጤና መድህን፣ በእናቶች እና ህጻናት የጤና አገልግሎት ውጤት የተመዘገበባቸው ስለመኾናቸው ተናግረዋል። የዲጅታል ሥርዓትንም ለመተግበር ጥረት እየተደረገ ስለመኾኑ ጠቁመዋል።
በቀጣይም የመጡትን የጤና ሥርዓት መሻሻሎች በማጠናከር ጤናማ፣ አምራች እና የበለጸገ ማኅበረሰብ ለመገንባት በቁርጠኝነት እንደሚሠራ ተናግረዋል።
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እንደተናገሩት በዲጅታል 2030 በጤናው ዘርፍ የዲጅታል ሥርዓትን እውን በማድረግ በውጤታማነት ለመፈጸም እየተሠራ ነው።
ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር በማስተሳሰር በጤናው ዘርፍ የተቀመጡት ግቦች በስኬታማነት እንዲተገበሩ ሳይንሳዊ በኾኑ አመልካቾች እየተመሩ ነው ብለዋል።
ለዚህም በእቅድ እና በሪፖርት ሥርዓት፣ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ በሀብት አጠቃቀም ዙሪያ፣ በሪፎርም ሥራዎች ከክልሎች ጋር በመምከር እየተሠራ ነው ብለዋል። በሁሉም አካባቢ ተደራሽ የሚኾን የጤና አገልግሎት ሥርዓት ለመዘርጋት ትኩረት ተደርጓል።
እንደ ሀገር በጤናው ዘርፍ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ትኩረት ተደርጓል ነው ያሉቱ የጤና ሚኒስትሯ። በዚህም በራስ አቅም የፋይንንስ ምንጭን በማስፋት በውጤታማነት መተግባር ይገባል ነው ያሉት።
በቀጣይ የተግባር አፈጻጸምን በጋራ እየገመገሙ በመሥራት፣ የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ፣ የበጀት አፈጻጸም ሥርዓትን የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ5 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከማዕድን ወጪ ንግድ ተገኝቷል ።
Next articleአረንጓዴው ሀብታችን – ከተራቆተ መሬት እስከ ቢሊዮን ዶላር ገቢ!