
የሕወሃት የፖለቲካ ጉዞ ከተመሠረተበት የደደቢት በረሃ ጀምሮ በአማራ ሕዝብ ላይ በረቀቀ የጥላቻ ትርክት እና ሰነድ የተቃኘ ነው። ቡድኑ የማዕከላዊ መንግሥቱን ሥልጣን በተቆጣጠረበት ወቅት ይህንን ስልታዊ የጥፋት ሰነድ በመዋቅራዊ መንገድ ተፈጻሚ አድርጎታል።
በዚህም በአማራ ሕዝብ ላይ ከባድ ሰቆቃን አድርሷል። በመላው ኢትዮጵያም የማይሻር የታሪክ ጠባሳን ጥሎ አልፏል። ሀገሪቱንም ለማያባራ የእርስ በርስ ግጭት እና የብጥብጥ ፈንጂ አጥምዶ ለምስቅልቅል ዳርጓታል።
በ2013 ዓ.ም የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ከጀርባ በመውጋት የጦርነት እና የጥፋት ጉዞውን በይፋ ጀመረ። በዚህም ሳቢያ ለዓመታት ባካሄደው የቡድኑ ወረራ ቀጥተኛ ሰለባ የኾነው የአማራ ክልል ነበር።
ቡድኑ በአማራ ክልል በፈጸማቸው ወረራዎች ላይ ታሪክ የማይረሳው መጠነ ሰፊ የዘር ማጥፋት፣ የጅምላ ጭፍጨፋ፣ የአስገድዶ መድፈር እና የቁሳዊ ውድመት ወንጀሎችን ፈጽሟል። በተለይም በማይካድራ፣ በጭና፣ እና በቆቦ አጋምሳ የተፈጸሙት የጅምላ ጭፍጨፋዎች የቡድኑን የጭካኔ ጥግ የሚያሳዩ ማረጋገጫዎች ናቸው።
📌 የዓለም ዓቀፍ ተቋማት የሰጡት ማረጋገጫ:-
አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ በአውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2021 እና በ2022 ባወጧቸው ሪፖርቶች ጅምላ ጭፍጨፋውን አረጋግጠዋል።
✍️በወቅቱ አሶሺየትድ ፕረስ የአካባቢውን ነዋሪዎች ጠቅሶ በሠራው ዘገባም በቆቦ እና አጋምሳ ብቻ የሟቾች ቁጥር ከ600 በላይ እንደሚደርስ ይፋ አድርጓል።
✍️ ኢሰመጉ በ2014 ዓ.ም ባወጣው የምርመራ ሪፖርት እንዳረጋገጠው በማይካድራ እና አካባቢው ከ1 ሺህ 100 በላይ ንጹሐን በሕወሃት ቡድን አባላት በጅምላ ተገድለዋል።
✍️ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም በየካቲት/2015 ዓ.ም ባሳተመው ጥናት እንደሚያመላክተው ቡድኑ በወረራቸው አካባቢዎች ከፍተኛ ጥፋት አስከትሏል።
📌 ሰብዓዊ ውድመት:- በጥናቱ እንደተመላከተው:
👉 ከ837 ሺህ በላይ ንጹሐን ዜጎች የሕወሃት ወረራ ጥቃት ሰለባ ኾነዋል፤
👉 ከ7 ሺህ በላይ ንጹሐን ሕይወታቸውን አጥተዋል፤
👉ከ18 ሺህ 400 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤
👉1 ሺህ 939 ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ተፈጽሞባቸዋል፣
👉7 ሺህ 462 የሚኾኑት በኃይል ታፍነው ተወስደው ደብዛቸው ጠፍቷል።
📌 ቁሳዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውድመት:-
በሕወሃት ወረራ ከ291 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ውድመት ማድረሱንም በጥናቱ ተረጋግጧል።
የገንዘብ መጠን ክልሉ በ2013 በጀት ዓመት ከነበረው የ62 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ዓመታዊ በጀት አንጻር ሲሰላ የአራት ዓመት ተኩል በጀቱን ሙሉ በሙሉ ማጣት እንደማለት ነው።
📌 የጥልቁ ክህደት እና “ያልተቀደሰው ጋብቻ”⚠️
አስገራሚው ነገር ዛሬ ላይ “ለአማራ ሕዝብ እንታገላለን” የሚሉ የታጠቁ ኃይሎች ከዚህ የጥፋት ኃይል ጋር የጥቅም ትብብር መፍጠራቸው ነው።
በተለይም ራሱን አፋብን ብሎ የሚጠራው ቡድን መሪዎች ገና ከአማራ ሕዝብ ደም እና እንባ ካልታጠበው ሕወሃት ጋር ቅንጅት ፈጥረው እንደሚሠሩ በይፋ መግለጻቸው ከራሳቸው አንደበት ተሰምቷል።
ይህ ተግባር በአማራ ሕዝብ ቁስል እንጨት ከመስደድ እና ሕዝቡን ደጋግሞ የመውጋት ያህል ክህደት ነው። ግብፅን እና ሻዕቢያን የመሣሠሉ የኢትዮጵያ ጠላቶችን አስተባብሮ ሀገር ለማፍረስ ከሚዶልተው የሕወሃት ስብስብ ጋር አብሮ ለመሥራት የሚደረግ ጥምረትም ፍጹም የሀገር ክህደት እና “ያልተቀደሰ ጋብቻ” ነው።
📌 ያልተቋረጠው የመንግሥት የሰላም ጥሪ🕊️
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተደጋጋሚ እንደገለጹት ኢትዮጵያን ለመውጋት የሚጥሩ የውጭ ኃይሎች ምኞት ከንቱ ቅዠት ነው። አሁን ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት ጦርነት ሳይኾን ሰላም እና ልማት ነው ብለዋል።
በሀገር ውስጥ ላሉት የታጠቁ ኃይሎች ከጦርነት ይልቅ የውይይት እና የትብብር መንገድን እንዲመርጡ ጥሪ አቅርበዋል። መንግሥትም ለማንኛውም የሰላም አማራጭ በሩ ክፍት መኾኑን በድጋሚ አረጋግጠዋል።
#አሚኮ #peace #Ethiopa
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_12_2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
