የወምበርማ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢው ለተሰማራው የጸጥታ ኀይል የዕርድ ሰንጋ ድጋፍ አደረጉ።

3

 

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን የወምበርማ ወረዳ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰላም እና ጸጥታን በማስከበር ላይ ለሚገኙት በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ ሬጅመንት እና ለወረዳው የጸጥታ አካላት የዕርድ ሰንጋ ድጋፍ አድርገዋል።

በድጋፉ ላይ የተገኙት የወምበርማ ወረዳ የአረበጋሬ እና የሊማ ቀበሌዎች አሥተዳዳሪ በእውነቴ ነበረ ሠራዊቱ እና የጸጥታ ኀይሉ ለሀገር እና ለሕዝብ ሲሉ ያለምንም ዕረፍት እየፈፀሙት ያለውን ሀገራዊ ግዳጅ ሕዝቡ በሙሉ ልብ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

ይህ የተጀመረው የድጋፍ ተግባር ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

አሥተዳዳሪው አክለውም ይህ ዓይነቱ የሕዝብ ተነሳሽነት በአካባቢው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፣ የሕዝብ እና የጸጥታ ኀይሎች ትብብር እንዲጠናከር እንዲሁም ሀገራዊ ግዴታን በጋራ ለመወጣት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የኅብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ መኾኑን ማሳያ ነው ብለዋል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የምሥራቅ ዕዝ ሬጅመንት አዛዥ ሻምበል አወል ስዒድ በበኩላቸው የአረበጋሬና የሊማ ቀበሌ ነዋሪዎች ያደረጉት አስተዋጽኦ ማኅበረሰቡ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን በጽናት መቆሙን የሚያሳይ ግልጽ መልዕክት መኾኑን አብራርተዋል።

“ሕዝባችን ያሳየን ፍቅር፣ ዕምነት እና ድጋፍ ለእኛ ትልቅ ሞራል ነው። መከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ሠራዊት ነው፤ ሕዝብን ለመጠበቅ እና ሰላምን ለማስከበር የሚከፍለው መስዋዕትነት የማይቋረጥ ነው” ብለዋል።

በዕለቱ የተገኙት የማኅበረሰብ ተወካዮች ሰላም የሁሉም መሠረት መኾኑን በመጥቀስ፣ መከላከያ ሠራዊት እና የጸጥታ አካላት እየከፈሉ ያሉትን መስዋዕትነት እንደሚያደንቁ ገልጸዋል።

የምሥራቅ ዕዝ እንዳለው አስተያየት ሰጭዎቹ የተደረገው የዕርድ ሰንጋ ድጋፍ የሕዝብ እና የመከላከያ ሠራዊትን ጠንካራ ግንኙነት፣ ለሀገር ሰላም እና ደኅንነት ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት እንዲሁም በችግር ጊዜ አንድ ኾኖ የመቆም ዕሴትን በጉልህ የሚያንፀባርቅ ነው።

#አሚኮ_ዜና #ድጋፍ_ለሠራዊቱ_ምዕራብ_ጎጃም #አማራ_ክልል

#ፍኖተ_ሰላም፡ ሐምሌ11/2018 ዓ.ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበምዕራብ ጎጃም ዞን በበቆሎ ሰብል ከ9 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።