🔥 የኢትዮጵያን መፍረስ የሚመኙ ታሪካዊ ጠላቶችን ምኞት ያመከነው ታላቁ ጉባኤ!

6

 

ኢትዮጵያውያን ውይይትን አስቀድመዋል፤ ለችግራቸው ዘላቂ መፍትሔ ሊያስቀምጡ🏢 በአዳራሽ ውስጥ ተሠባሥበዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የኢትዮጵያ ሕዝቦች ድምጽ፤ የልዩነታቸው መፍቻ ቁልፍ፤ የሀገራቸውን መጻኢ ዕድል የሚወስኑበት፤ በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ሥርዓትን የሚገነቡበት፤ በራሳቸው ለራሳቸው የተዘጋጀ ታላቅ ጉባኤን እያካሄደ ነው።

የኢትዮጵያውያን መሠባሠብ፤ በአንድነት መቆም፤ ልዩነታቸውን የብዝኃነት መገለጫ ለማድረግ፤ ለዘላቂ ሰላማቸው፤ ለአብሮነታቸው፤ ለኢኮኖሚያዊ ዕድገታቸው መሠባሠባቸው ለታሪካዊ ጠላቶቻቸውን ሰላም ነስቷቸዋል።

🇪🇹 የኢትዮጵያ ስኬት፤ ዘላቂ ሰላም፤ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት፤ አፍሪካዊ ተደማጭነት፤ የኢኮኖሚ ዕድገት እና ተደራሽነት እንደ እግር እሳት የሚለበልባቸው የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የሄደበትን ርቀት ለማሳነስ የሀሰት መርዛቸውን መርጨት ጀምረዋል።

ለወትሮም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ለሰከንድ የማያንቀላፉት ጠላቶች የውስጥ ባንዳዎችን በመጠቀም የምክክር ጉባኤውን ስኬት ለማደናቀፍ ሲጥሩ ቆይተዋል። በሕዝብ ድምጽ፤ በሕዝብ ጥያቄ፤ በሕዝብ ይሁንታ የተቋቋመው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ግን በይፋ ምክክሩን አስጀምሮ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና ሁለንተናዊ ዕድገት እየመከረ ነው። የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራም አክሽፏል።

ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በሕዝብ ባለቤትነት እየተመራ፤ የሕዝብ አጀንዳን አቅፎ የያዘ፤ እንደ አንድ ተሳታፊ መንግሥት የራሱን አጀንዳ እንዲያቀርብ ዕድል የሰጠ በኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያውያን የተቋቋመ የሕዝብ ድምጽ ነው።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አጀንዳዎችን ይፋ ባደረጉበት ወቅት አጀንዳዎቹ ከሕዝብ ፍላጎት፤ ተስፋ እና ስጋት የተቀዱ ናቸው ብለዋል።

🇪🇹 ሁሉም ኢትዮጵያውያን ትርጉም ያለው ተሳትፎ በማድረግ ድምጻቸው ተካቷል ነው ያሉት። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያውያን የሕዝብ ድምጽ መኾናቸውን አረጋግጠዋል።

ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጉባኤ ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግርም ጉባኤው እርስ በእርስ እንድንደማመጥ፤ የሌላውን ሕመም እንድንረዳ፤ በየጊዜው የሚያመረቅዙ ትርክቶች እና የታሪክ ጠባሳዎች እንዲሽሩ የተዘጋጀ የሕዝብ ድምጽ ነው ብለዋል።

የምክክር ኮሚሽኑ ሂደት አካታች እና ፍትሐዊ እንዲኾን አርሶ አደሮች፤ አርብቶ አደሮች፤ ሴቶች፤ ወጣቶች የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ ተቋማትና ማኅበራት፤ ምሁራን እና የማኅበረሰብ መሪዎችን በታማኝነት እና በገለልተኝነት የመለየት ሥራ ተከናውኗል ነው ያሉት።

📢 በሕዝብ ድምጽ የተቋቋመው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የአሠራር ሥርዓትን በመዘርጋት፤ ሕጋዊነት እና ተዓማኒነት እንዲኖር በማድረግ፤ ግልጽነትን በማስፈን፤ ተሳታፊዎችን የመለየት፤ አጀንዳን በማሰባሰብ እና በመቅረጽ፤ ግንዛቤን በመፍጠር ስኬታማ እንዲኾን መሠራቱን ገልጸዋል።

ለኢትዮጵያ በሕዝብ ድምጽ የተመሠረተ ታማኝ፤ አካታች፤ግልጽ እና ሳይንሳዊ ምክክር ማድረግ ፍቱን መድኃኒት መኾኑንም ተናግረዋል። ሕዝቡ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ባለቤት መኾኑን ለማሳወቅ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውንም ገልጸዋል።

#አሚኮ #ሀገራዊምክክር #National_Dialogue #ኢትዮጵያ🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_10_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article📢 የሀረሪ ክልል ምክር ቤት ለበጀት ዓመቱ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ።🎉
Next article🇪🇹የሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎች የማንም ሳይኾኑ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድምጾች ናቸው።