የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ለምን ተቋርጦ ቆየ?

5

 

ባሕር ዳር: ሐምሌ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሃምሳ ዓመታት በፊት ጀምሮ ወደ ደብረ ማርቆስ የበረራ አገልግሎት ሲሰጥ ነበር። ነገር ግን ባለፉት ሃያ ዓመታት ይህ አገልግሎቱ ተቋርጦ ቆይቷል።

ምክኒያቱ ምን ነበር?

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራ አሥፈጻሚው መስፍን ጣሰው የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ተቋርጦ የቆየው አየር መንገዱ የመደባቸውን ትላልቅ አውሮፕላኖች ማሳረፍ ባለመቻሉ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትልልቅ አውሮፕላኖችን ለሀገር ውስጥ በረራ የመደበው አገልግሎቱን ሲሰጡ የነበሩት ዳሽ 6 (dash 6) የተሰኙ አውሮፕላኖች ከአገልግሎት ውጭ መደረጋቸውን ተከትሎ ነው።

የኢትዮጵያ አየር መንገድም ወደ ማርቆስ ያደርግ የነበረውን በረራ በዚህ ምክኒያት ለበርካታ ዓመታት አቋርጦ ቆይቷል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleወጣቶችን ለጦርነት በዶላር እየሸጠ የሚገኘው ሕገወጡ የሕወሓት ቡድን!