“አሁን ያለው ትውልድ ባለፉት ዓመታት የነበሩ ችግሮችን ዘክሮ እና መክሮ መፍታት አለበት” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

5

 

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ሥብሠባውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በተገኙበት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱት ጥያቄዎችም ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማብራሪያቸው እንደገለጹት የሀገራዊ ምክክሩ ከታች ጀምሮ የተደረገ ስለኾነ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይኾን ለአፍሪካም ጠቃሚ ነው ብለዋል።

በሀገራዊ ምክክር እንወያይባቸው እየተባሉ ያሉ ጉዳዮች የብልጽግና ፓርቲ ሀሳቦች አለመኾናቸውን ነው ያብራሩት። ለአብነት አማራ እና ትግራይ አካባቢ የተፈጠረውን የወሰን እና የማንነት ችግር ብልጽግና ፓርቲ አልፈጠረውም፤ ችግሮች ብልጽግና ፓርቲ ላይ ወደቁበት እንጂ፤ ብልጽግና ፓርቲ የተፈጠሩ እና እየተንከባለሉ የመጡ ችግሮችን እንፍታ ነው ያለው፤ አሁን ያለው ትውልድ ባለፉት ዓመታት የነበሩ ችግሮችን ዘክሮ እና መክሮ መፍታት አለበትም ብለዋል።

የምክክሩ ሂደቱ ታስቦ እና ታቅዶ እየተከናወነ ያለ ሂደት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክክር ጉባዔው የሚነሱ መሻሻል ያለባቸው ጉዳዮች ተሻሽለው እንደሚጸድቁ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

#አሚኮ_ዜና #የምክር_ቤት_ውሎ #PMAbiyAhmed #Parliament

በሮዛ የሻነህ

#ባሕር_ዳር_ሰኔ_30_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ባለፉት ዓመታት ከ4ሺህ በላይ የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next article“የነገዋን ኢትዮጵያ የሚገነባው የትምህርት ኢንቨስትመንት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)